የአጭር የመካከለኛና…

የአጭር የመካከለኛና…

  • Post comments:0 Comments
የአጭር የመካከለኛና የረጅም አመት እቅድና ግብ አለን፡፡ ከግባችን የሚያሰናክለን አንድም ሀይል አይኖርም፡፡ የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ከመፍታት አልፈን አገራችንን የብልጽግና ተምሳሌት እንደምናደርጋት አንጠራጠርም፡፡
 
ኢትዮጵያ ዜጎች በሰላም የሚኖሩባት፣ የደህንነትና የጸጥታ ስጋቶች ተወግደው የሰላም አየር የሚነፍስባት እንድትሆን የተጀመረውን የተቀናጀ ህግ የማስከበር ሥራ አጠናክረን በመቀጠል በሁሉም የአገሪቱ ክፍል የህግ የበላይነት እንዲከበር እናደርጋለን፡፡ ለዚህም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የዘንድሮው አገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን እጅግ ወሳኝ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ማድረግ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መረባረብና ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል፡፡
 
ኢትዮጵያ የሁላችንም አገር ናት፡፡ በተለያዩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ ቄዬያቸው በመመለስ እንዲቋቋሙና ወደ ቀደመው መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ አጀንዳው ነው፡፡ ይህ እንዲሳካና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች አጋሮች በአንድነት ሊተባበሩ ይገባል፡፡
 
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCDjrabrExOjDbogAkeOUI5w
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

Leave a Reply