ብልጽግና ራሱን በአዳዲስ አስተሳሰቦች እየለወጠ ሀገርን ከፈተና ማቅ አውጥቶ ከፍታ ለማሻገር እየታተረ የሚገኝ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ምንጊዜም የኢትዮጵያን ስኬቷን ሳይሆን ውድቀቷን፣ከፍታዋን ሳይሆን የቁልቁለት ጉዞዋን፣ጥንካሬዋን ሳይሆን ድክመቷን የሚመኙ እንቅልፍ የሌላቸው ጠላቶች ዛሬም ድረስ እ ንቅፋት መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡
ሕዝባችን ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሀገር ሰላምና ልማት በጥቅሉ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያሳዬ ያለው ፍላጎት ከጊዚያዊ ግጭቶች ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አንሶ አያውቅም፡፡
የኢትዮጵያዊያን የመልማት ፍላጎት በሌሎች ሃገራት ይሁንታ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ከድህነት ጋር ተጣብቆ መኖር በቅቶናል፤እጃን እስኪሻክር ድረስ ሌት ተቀን ሰርተን መለወጥ ያሻናል፤ይህን ለማድረግ ተፈጥሮ የሰጠችንን ጸጋዎች ተጠቅመን የመልማት ሙሉ መብት አለን፡፡
የዛሬ ሶስት ዓመት ሃገሪቱ ወደለዬለት ግጭትና ትርምስ አልፎም የሀገሪቱ ህልውና ጥያቄ ውስጥ በወደቀበት ሰዓት ብልጽግና ፓርቲ ሃገሪቱን ከትርምስና ከብተና በማዳን በህዝብ ዘንድ ይበልጥ ከበሬታን ያገኘ ፓርቲ ነው፡፡አሁንም ከሶስት ዓመታት በኋላ መልካቸው የተቀዬረ ቢመስልም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ስንጀምር ሃያልነታቸውን ሊያሳዩን፣ሊያስፈራሩን እና ጫና ሊያሳድሩብን ላይ ታች ማለት ጀምረዋል፡፡ ዳሩ ከህልም የዘለለ ባይሆንም፡፡
ብልጽግና ከባድ እና ህዝባዊ ሀላፊነትን የተሸከመ ፓርቲ ነው፡፡የተሸከመውን የህዝብ አደራ መወጣት የሚያስችሉ በሳልና ጊዜውን የዋጁ አመራሮችንም ስለመያዙ ጥርጥር የለውም፡፡ከላይ እስከ ታች ያለው የፓርቲው አመራር ሀገራዊ እሴቶችን በተሟላ መልኩ ለማስቀጠል ትልቅ ኃላፊነት ያነገቡ ጽኑ አመራሮች ናቸው፡፡
በትንንሽ ኮሽታዎች የማይደናገጡ ይልቁንም የተጣለባቸውን ህዝባዊ አደራ ለመወጣት መስዋዕት ለመክፈል የተዘጋጁና እየከፈሉ ያሉ የአመራሮች ስብስብ ነው-ብልጽግና፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን ዘመናትን ተሻግረን ዛሬ ላይ የደረስነው ከሚለያዩንና ለግጭት ከሚያበቁን መንስኤዎች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ብዙ ሺህ ምክንያቶች መኖራቸውን ስለተገነዘብንና በአንድነት መቆም በመቻላችን ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሆነን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የኛን ትርምስ ለሚናፍቁ ሃይሎች በአንድነታችን አንገታቸውን ልናስደፋቸው ይገባል፡፡
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ