You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments
“ብልፅግና የሁሉም ሰው ራዕይ ሊሆን ይገባል።” – አቶ መለሰ ዓለሙ
በየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩት አቶ መለሰ ዓለሙ ከክፍለ ከተማው ወጣቶች ጋር መጪውን ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ ።
በውይይት መድረኩ ላይ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክና የበርካታ ስልጣኔዎች ባለቤት መሆኗን የጠቀሱት አቶ መለሰ በቀጣይም የአፍሪካ ብልፅግና
ተምሳሌት በማድረግ የአድዋው የይቻላል መንፈስ ዳግም እንደሚረጋገጥ አስረድተዋል።
ሀገራዊ ህብረብሄራዊ ፓርቲ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የሚያበለፅግና የሚያሻግር ሀሳብ እንዳለው በተግባር ማሳየት መጀመሩን የገለፁት አቶ መለሰ እንደ ግለሰብም ለመጭው ትውልድ የብልፅግና አሻራቸውን አስቀምጠው ለማለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ለወጣቶች አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም አከባቢያችንን በመለወጥ ከተማችንና አገራችንን እናበለፅጋለን ያሉት ሀላፊው ለወጣቶችና ለሴቶች ልዩ ትኩረት የሰጠውንና በወንድማማችነት ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርገውን ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም ብልፅግና ፓርቲ በተግባርም እኩል ተጠቃሚነትን እየገነባና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እያቃለለ ህዝብን ማዳመጥ መጀመሩን መስክረዋል። ለላቀ ስኬት ከብልፅግና ጎን እንደሚሰለፉም አረጋግጠዋል።
በቀጣይም የከተማችንና የሀገራችንን ተስፋ የሚያለመልመው ብልፅግና ፓርቲ በመሆኑ የምርጫ ምልክቱ የሆነውን አምፑልን ወጣትቹ ለአቶ መለሰ በስጦታ መልክ አበርክተውላቸዋል ።

ምላሽ ይስጡ