You are currently viewing ቦርዱ ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ

ቦርዱ ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ

  • Post comments:0 Comments
ቦርዱ ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ
ግንቦት 28 ቀን ሊካሄድ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የምርጫ ሂደቱ በሁሉም የመራጮች ምዝገባ በተጠናቀቀባቸው ቦታዎች ብቻ ነው ተብሏል።
ከመራጮች ምዝገባ ጋር አቤቱታ የተነሳባቸው እና ምዝገባውን ዘግይተው የጀመሩ እና ያላጠናቀቁ የምርጫ ክልሎች እና ጣቢያዎች ላይ ግን በዚሁ ቀን አይካሄድም ነው የተባለው።
ምዝገባው ከተቀመጠለት ቀን ዘግይቶ ለመካሄዱ ምክንያት ደግሞ ምርጫ ቦርድ ማከናወን ያለበትን ስራ ለማጠናቀቅ ፣ ሎጅስቲክስ እና ቁሳቁስን ለማዳረስ፥ምርጫው በአንድ ቀን መካሄድ እንዲችል ለማድረግ አስፈላጊ እና ተጨማሪ የምርጫ አስፈፃሚ ቁጥሩን ለመጨመርም በማሰብ መሆኑ ተመላክቷል።
እስካሁን ከ138 ሺህ 350 በላይ አስፈፃሚዎች በተጨማሪ ከ106 ሺህ 345 በላይ የሰው ሃይል ለማካተትም በመሰራት ላይ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ምላሽ ይስጡ