ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሳምንት መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ካስተላለፉት መልዕክት መካከል በጥቂቱ
******************************************************************************************************
ኢትዮጵያ የሁላችንም የኩራት ምንጭ ስለሆነች እኛ ኢትዮጵያዊያን በሃገራችን የምንኮራ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ሃገራት የኩራትና የጀግንነት እንዲሁም ብልጽግና ምሳሌ በመሆን በአህጉራችን ያለውን ድህነትና ችግር ለመቅረፍ ዛሬም እንደትናንቱ ሃገራችን ፈር ቀዳጅ ሆና ስራዋን እንደምትጀምርና መፈጸም እንደምትችል የማናሳይበት በር መክፈቻ ነው፡፡
ብዙ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያን አያውቋትም፤ኢትዮጵያ በእያንዳንዱ ክልል፣ዞንና ወረዳ ብዙ ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ በአንድ ኢትዮጵያዊ ማንነት የተገመዱ የሚያስደንቅ የታሪክ፣የባህል፣የሀብት ትስስርና አንዱ ለአንዱ ግብዓት ካልሆነ ብቻውን ለመቆም የተሟላ ጸጋ ለማግኘት የማይቻልበት መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያን በመልበስ ክብርና ዝናዋን መልሰን ለሚያውቁም ለማያውቁም የምናጎናጽፍበት ሳምንት እንዲሆን፣በእያንዳንዳችን ክልል የሚገኘውን ሃብት በማወቅ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ በጋራ እንድንሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
በመጨረሻም ሁላችንም እንደምናውቀው ሃገራችን ከሚለው ቋንቋ ወጥተን ኢትዮጵያ የሚለውን ቋንቋ ከጀመርን በኋላ በእያንዳንዱ ንግግር ውስጥ ቢያንስ በርከት ላለ ጊዜ ደጋግመን የምንጠራው የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የኩራትና የነጻነት ምንጭ የሆነው ስም በእያንዳንዳችን አፍ ውስጥ ተለምዷል፤ሰው በሰማውና ባየው ነገር ስለሚቀረጽ ኢትዮጵያን ማለት እንደ አበባ የምታምር፣ኢትዮጵያ ማለት ለነጻነትና ለክብሯ የማትደራደር ሃገር መሆኗን ለማዬት ለማሳዬት ለመማር ለማስተማር በእጅጉን የሚያግዝ ጊዜ መሆኑን ተስፋ አደርጋለሁ፣ምናልባት ኢትዮጵያን ሳታውቁ የምትሞካክሩን አንዳንድ ያልገባችሁ ሰዎች ካላችሁም የኩራትና የድፍረታችን ምንጭ ራሷ ኢትዮጵያ ናት፡፡
አመሰግናለሁ !