You are currently viewing ሁሉም የሚሳተፍበት የብዝሃን ኢኮኖሚ…

ሁሉም የሚሳተፍበት የብዝሃን ኢኮኖሚ…

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና ፓርቲ ዜጎች በዛሬ ድህነት ውስጥ ሳይሆን ነገ በተሻለ ሁኔታ ፍላጎቶቻቸው ተሟልቶላቸውና ጥራት ያለው ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ተቀዳሚ ግቡ ነው፡፡በተለይም በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖረው ለብዙ ጊዚያት በፍጆታው ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ ያላሳየው ህዝባችን በተለየ ሁኔታ ከድህነት ለማውጣት ይሰራል፡፡
አጠቃላይ ድህነትን በግማሽ በላይ ለመቀነስ መስራት የጉዟችን ተቀዳሚ መዳረሻ ነው፡፡ይህም ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ፍላጎቶችን የማሟላት ግብ የብዙሃን የኢኮኖሚ ተዋንያንን መስተጋብር እንዲሁም ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ይጠይቃል፡፡
ሁሉም የሚሳተፍበት የብዝሃን ኢኮኖሚ የጋራ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ነው፡፡በዚህም ፓርቲያችን የኢኮኖሚ ተዋንያን ተሳትፎ የሚጨምር እና ምርታማነት የሚያረጋግጥ ስራዎችን በአንድ በኩል በትኩረት ሲሰራ በሌላ በኩል የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይንቀሳቀሳል፡፡
ሃገራችን ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ሃገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን መሰረት በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ይሰራል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናችን ሰው ተኮር ሲሆን ለዚህም ሁሉም የልማት ስራዎቻችን በዜጎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ በትኩረት ይሰራል፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ