እኛ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በወንድማማችነት ያስተሳሰሩ የማንነት መገለጫዎች፣ ዓለምን ያስደመሙ ድንቅ እሴቶች፣ ባህልና ወጎች ያሉን ህዝቦች ነን፡፡ ይህ ዓለም የሚመሰክረው ዘመናትን የተሻገረ የእኛ እውነት ነው፡፡ እነዚህን እሴቶች ይዘን ዛሬያችንን በማጽናት፤ ነጋችንን ደግሞ እንገነባለን፡፡
ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት፡፡ በዚህ የጋራ ቤታችን ወንድማማችነትን አንግሰን የአንድነት መንፈሳችንን አድሰን የዛሬ ችግሮቻችንን ሁሉ በእውነት ሃያልነት አሸንፈን፣ በጥበብ እንሻገራለን፡፡
እኛ ብልጽግናዎቸ ሁሌም ቃላችንን እናከብራለን፤ ለዚህ ቅንጣት ጥርጥር የለንም። በፈተናዎች ብንከበብም፣ በችግር ሸለቆ ውስጥ ብናልፍም፣ ሜዳው ዳገት እንዲሆንብን የሚተጋ ኃይል ቢኖርም ቃላችንን እናከብራለን። እኛ ብልጽግናዎች ቃላችንን ነን።