You are currently viewing ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና

ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና

  • Post comments:0 Comments

ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም በተለያዬ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ የገባችበት ጊዜ ላይ ብትሆንም እንኳ የተጀማመሩ በርካታ ሀገራዊ ልማቶች ያለ ምንም እክል ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያለ የድንበር ውዝግብና ታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ ያለው እሰጣ ገባ ከውስጣዊ ተግዳሮቶች ጋር ተዳምሮ ልማታችንን በተፈለገውን ፍጥነት ልክ እንዳይቀጥል እንቅፋት ቢሆንም ብልጽግና ፓርቲ የትኛውንም አይነት ጫና ተቋቁሞ ለቆመለት የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና ሀገራዊ ህልውና መረጋገጥ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ብልጽግና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና በሚል በያዝነው ዓመት የሚካሄደውን ምርጫ ነፃ፣ሰላማዊ፣ፍጹም ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ምርጫ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ግብ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል፡፡ሆኖም ግን ከውድ ሀገራቸው ዘላቂ ጥቅም ይልቅ ጊዚያዊ የግል ጥቅማቸው የቀደመባቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች ምርጫውን ለማስተጓጎል እና ደካማና እንደፈለጉ የሚያዙት መንግስት ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ መሆናቸውን ኢትዮጵያዊያን ተገንዝበን አንድነታችንን ይበልጥ ልናጠናክር ይገባል፡፡

አገሪቱን የማንም መፈንጫ ለማድረግ እና ጎንበስ ቀና እያለ ለውጭ ሀገራት ታዛዥ የሆነ ደካማ መንግስት በመፍጠር ጥቂቶች ብቻ ያሻቸውን እያደረጉ የሚኖሩባት ሀገር እንድትኖር ምርጫውን ሲሻቸው ያጣጥሉታት ሌላ ጊዜ ደግሞ በለዘብተኝነት ይመለከቱታል፡፡ያም ሆነ ይህ  ምርጫው በተቀመጠለት ቀነ ገደብ መካሄዱ አይቀሬ ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ