ብልጽግና ፓርቲ በ2013 የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ባለፉት ሶስት ዓመታት ጀምሮ ምርጫው በህዝቡ ዘንድ ፍጹም ተአማኒነትን ያተረፈ፣ነጻና ፍተሃዊ ምርጫ ለማስኬድ እንዲሁም በምርጫው ማንም ያሸንፍ ማን ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል በጥቅሉ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ፓርቲው ያለውን ቁርጠኝነት ሲገልጽ ቆይቷል፡፡
እርግጥ ነው ዘንድሮ በሚካሄደው ምርጫ ዜጎች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በሚኖራቸው የነቃ ተሳትፎ ምክንያት የሚደርስባቸው ግድያም ሆነ እስር፣ ስቃይም ሆነ ስደት፣አድሎም ሆነ መገለል ሊኖር አይችልም፤ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችል የፍትህ ስርዓት ጉድለት እንዳይኖር ብልጽግና ፓርቲ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፤
ለምርጫው ፍጹም ሰላማዊነት የሁላችንም ድርሻ የጎላ ነው፤ሀገር ህልውናዋ ተጠብቆ እንደ ሀገር ትቀጥል ዘንድ የመራጭነት ካርድ ዛሬውኑ በማውጣት ለምርጫው ስኬታማነት የጋራ ርብርብ እናድርግ፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ