የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል ፈጥርን በዓል በሰላምና በአንድነት እንዲያከብር ጥሪ አስተላለፉ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ 1442ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላምና በአንድነት እንዲያከብሩ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉንም ከሌላቸው ማህበረሰብ ጋር በጋራ ማክበር እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
በዛሬው ዕለትም የኢፍጣር ስነ ስርዓት በጎዳና ላይ እንዲደረግ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈቃድ መገኘቱንም ገልጸዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው ሰላም እንዲጠበቅ ለፈጣሪ ዱአ እንዲያደርግና አንድነቱንና ልማቱን እንዲያጠናክርም ነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የገለፁት።
ዛሬ ማታ ጨረቃ ከታየች በዓሉ ነገ ረቡዕ የሚከበር ሲሆን፣ ዛሬ ማታ ካልታየች ግን በዓሉ ሐሙስ እንደሚሆን ነው ሀጂ ሙፍቲ በመግለጫቸው ያስታወቁት።