ኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ወሳኝ ሀገራዊ ኩነት ታስተናግዳለች ፡፡ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለስድስተኛ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ገዢው ፓርቲ ብልጽግናን ጨምሮ በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ አሸንፈው መንግስት መመስረት የሚያስችላቸውን የህዝብ ድምጽ ለማግኘት ቅስቀሳ ከጀመሩ ቆየት ብለዋል፡፡
ምርጫ ሻጭና ሸማችን የሚያገኛኝ የወቅቱ ገበያ ነው፡፡ሻጮች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲሆኑ ሸማቹ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝብን ድምጽ ለማግኘት ያስችለናል የሚሉትን ሀሳቦቻቸውን በተለያዩ ዘዴዎች አቅርበው ህዝብን ለማሳመን ጥረት ያደርጋሉ፡፡
ሸማቹ የኢትዮጵያ ህዝብም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይዘውት የቀረቡትን ጉዳዮች በማጤን በድምጽ መስጫ ቀን ይወክለኛል፤ሀሳቤን ያሟላልኛል፣ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ያጠናክርልናል፣በስሜት ሳይሆን በዕውቀትና በዕውነት ላይ ተመስርቶ ሀገርን ያስተዳድራል፣ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ የወጣና ወንድማማችነት የሚያጎለብቱ ስራዎችን ይሰራልኛል፤ኢትዮጵያን ከውስጥም ከውጭም የሚደርስባትን ጫና ተቋቁሞ ወደ ብልጽግና ከፍታ ያሸጋግራታል ብለው ዕምነትና ተስፋ በጣሉት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ድምጻቸውን ይሰጣሉ፡፡
አምፖልን ይምረጡ