• Post comments:0 Comments

ለመደማመጥ ሰከን ብሎ መነጋገር ያስፈልጋል፤ስክነትና ትዕግስት በሌለበት ትርጉም ያለው ቁም ነገር አይገኝም፡፡በማንኛውም የዕለት ተዕለት ስራ በፓርቲ ፖለቲካም ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች ሰከን ብሎ መነጋገር ይጠቅማል እንጂ ጉዳት የለውም፡፡


ዴሞክራሲ የተለያዩ ሀሳቦች በነጻነት የሚንሸራሸሩበት የሃሳብ ገበያ ስለመሆኑ ብዙዎችን የሚያስማማ ዕውነታ ነው፡፡ይህ ደግሞ የመነጋገርና የመደማመጥ አስፈላጊነት ያለውን ዋጋ ለማሳዬት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት በነበሩት መስተጋብሮችና ቋንቋዎች ሳይበግሩት በመግባባት ክፉና ደግ ዘመናትን በጋራ አሳልፈዋል፡፡
እምነትና የግል ፍላጎታቸውን እንዲሁም ባህሎቻቸውን በመከባበር እና በመተሳሰብ አቻችለው ሀገርን እዚህ አድርሰዋል፡፡የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻቸውን በጋራ ጠብቀው ለአሁኑ ትውልድ አስረክበዋል፡፡ማንነታቸው እየተከበረ ከትንንሽ ጉዳዮች ይልቅ ግዙፉን ኢትዮጵያዊ ምስል እያስቀደሙ ተደማምጠው አያሌ ዓመታትን በፍቅር እና በአንድነት ኑረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልገን መደማመጥ ነው፡፡በመደማመጥ ውስጥ ለጋራ ችግሮቻችን የጋራ መፍትሔ እናገኛለን፡፡በመደማመጥ ውስጥ የህዝባችን አንድነትና ወንድማማችነት ይጎለብታል፡፡ሁሉም ነገር በሰከነ መንገድ ተነጋግረን መደማመጥ ከቻልን የህዝብ ሰላምና የሀገርን ደህንነት ማግኘት እንችላለን፡፡
በእርግጥ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እርስ በእርስ ተነጋግረው መደማመጥና መግባባት ላይ እንዳይደርሱ የሚሹ ግለሰቦች፣ቡድኖች፣የፖርቲ ፖለቲከኞች፣ሊህቃን፣አንቂዎች…ወዘተ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡በህዝብ ሰላም እጦትና የሀገር ደህንነት ሲናጋ የግል ጥቅማቸው ከህዝብና ከሀገር የሚበልጥባቸው የሚመስላቸው የዋህ ሀይሎች ይኖራሉ፡፡


የዛሬ መደማመጣችን ነገ ለምንሻት የበለጸገች ኢትዮጵያ መሰረት ነው፡፡የቱንም ያህል እንቅፋቶች ከውጥም ሆነ ከውጭ ቢበዙብንም ተግዳሮቶችን ተነጋግረን በመደማመጥ አልፈን ከመዳረሻችን የብልጽግናና ማማ ላይ መድረሳችን አይቀሬ ነው፡፡

አምፖልን ይምረጡ

Leave a Reply