ነገር ግን ለታላቅ ደስታ የታጨ ሁሉ እስከመጨረሻው በጽናት ይጓዛል፤ ድልን ይጎናጸፋል ማለት አይደለም። በክርስቶስ የማዳን መንገድ የአዳም ዘር በሞላ ለደስታ ቢታጭም እንደ ይሁዳ ያሉት በመንገዱ ተሸንፈው ስለወደቁ የድሉ ባለቤት አልሆኑም።
ስለዚህ የተስፋ መንገዳችን በስኬት እንዲቋጭ ዛሬም ሆነ ነገ ፈተናውን በድል መወጣት ይኖርብናል። በየመንገዳችን የሚገጥሙን ፈተናዎች ወደ ተስፋ መሻገሪያ በሮቻችን ናቸው፡፡
ጥምቀቱና ስቅለቱ ለክርስቲያናዊው የቅድስና ጉዞ የመዳን በሮች እንደሆኑት ሁሉ እንደ ሀገር ለምናደርገው የዲሞክራሲ ጉዞ ከፊታችን የሚጠብቀን ምርጫ በድል ከተወጣነው አንዱ የተስፋ በራችን መሆኑ አይቀርም። ስለዚህ ሁላችንም ጥሩ ዝግጅት አድርገንና መንፈሳችንን አጽንተን በድል ልንሻገረው ይገባል፡፡