በምርጫ 2013 ላይ የተኮረ ውይይት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት እየተካሄደ ነው ።የምርጫ 2013 ፋይዳ ዋና ተዋናዮች እንዲሁም የምርጫ ስረአቱን በሚመለከት የውይይት የመነሻ ሀሳብ በጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ቀርቧል።
የቀረበው ፅሁፍ በዋናነት የ2013 ምርጫ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲ ሽግግር ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለውና በዚህም ሁለም የምርጫ ተዋናዮች ዜጎችም ጭምር የሚኖራቸው ተሳትፎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምን እንደሚጠበቅ ኢትዮጵያ የምትጠቀምውን የምርጫ ስርአቶችን ጨምሮ በዓለም ላይ ያሉ የምርጫ ስርአቶችን የዳሰሰ ነው።በቀረበው የመነሻ ፅሁፍ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት እያካሄዱበት ነው።