የምንገኝበት የፖለቲካ መድረክ ሀገር አፍራሽ ከሀዲዎች እየፈረሱ የሚገኙበት ታሪካዊ መድረክ ነው የግፈኞች ፀሀይ እየጠለቀች በምትገኝበት በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ወገን ከሀዲውና ወንበዴው ትህነግና የጥፋት አጋሮቹ በሌላ ወገን የሚፋለሙበት አውደውጊያ ላይ እንገኛለን።
ፓርቲያችን እና መንግስታችን ብስለት በተሞላበት አመራር የንጹሃንን ደም የጠጣው እና የህዝባችንና የሀገራችን አለኝታ የሆነው የመከላከያ ኃይላችንን የጨፈጨፈው አሸባሪ ቡድን በያለበት በማደን በሕግ ፊት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በክልላችን ከህወሃት ጁንታ ተላላኪዎችና ከኦነግ ሸኔ ተልዕኮ ወስደው የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ሀይሎችና የጥፋት ተልዕኮአቸውን ከሚደግፉ ርዝራዦቻቸው ሙሉ ለሙሉ ነፃ እስኪሆን ድረስ ሕግ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፓርቲው በመግለጫው ገልጻል።
የክልላችን ነዋሪዎች ሁላችንም የአካባቢያችንን ሰላም በንቃት በመጠበቅ ከከሀዲው የሕወሓት ጁንታ ተላላኪዎችና ከኦነግ ሸኔ ተልዕኮ ወስደው የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሠላም ሀይሎችን በየአካባቢያቹ ለሚገኘው የፀጥታ አካል በማጋለጥ እና ጥቆማ በመስጠት የማይተካ ሚናችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።