የሰላም ዘብ የሆነው የመከላከያ ሰራዊታችን በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ ሰላምና መረጋጋትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት በአፍሪካ ሀገራት ዘንድ ተመራጭ ሰራዊት አድርጎታል፡፡ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት ያለው ቁርጠኝነት፣በመንግስታት ዘንድ ያለው አመኔታ፣ጠላትን ለይቶ መዋጋት መቻሉ፣ ለሰላም የሚሰጠው ትኩረት፣ከራስ በፊት በሚለው መሪ ቃሉ እና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ሰራዊታችን ተፈላጊ አድርጎታል፡፡
በአጎራባች ሶማሊያ የመሸገውን የአልሸባብ የጥፋት ሃይል ጨምሮ የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሌሎች ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ዕውቅና ችረውታል፡፡
የመከላከያ ሰራዊታችን እንደ ጽንፈኛው የህወኃት ቡድን አይነት የአገርን ሰላም፣ልማትና መረጋጋት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ማንኛውንም የሽብርና የጥፋት ሃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል፡፡