ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል ። በዋናነት በትግራይ ክልል የተጀመረውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ አስመልክቶ የመንግሥትን አቋም ግልፅ አድርገዋል።
መንግሥት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ የጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ዓላማውን አብራርተዋል። በህግ ማስከበር ሂደት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት ለአገልግሎት ምቹ እና ነፃ መንቀሳቀሻ ኮሪደር መመቻቸቱን ገልፀዋል። በመጨረሻም የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ለአማካሪው አረጋጠውላቸዋል።