ይህ አጥፊ ቡድን በከተማችን ላይ በተለያዩ አከባቢዎች ሁከትና ግርግር ለመፍጠር በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቦንቦችን ከቆሻሻ ጋር አብሮ በመጣል ሰላማችንን ለማደፍረስ እየሰራ በመሆኑ ሁሉም የከተማችን ህብረተሰብ አከባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ እና የእነዚህ አጥፊ ሀይሎች ሴራ እንዲከሽፍ ሁሉም ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገልጿል ።ጁንታው የህወሓት ቡድን ሀገርን ለማተራመስ ያሴረው ሴራ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በመመከት ላይ ይገኛል ።
ይህን የጥፋት ሀይል በከተማችን የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችም ለሀገር ጸር የሆነውን አጥፊ ቡድን መንግስት የጀመረውን ህግን የማስከበር ዘመቻ ጎን እንዲሰለፉ እና ከሀገር መከላከያ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ ቀርቧል ።አመራሩም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊታችን የተጀመረው የድጋፍ ስራ አመርቂ ውጤቶች እየታዩ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገልጿል ።