You are currently viewing የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለጀግናውየሀገር መከላከያ ሰራዊት 240 የእርድ ሰንጋና 107 በጎችና ፍየሎች ድጋፍ አድርጎል

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለጀግናውየሀገር መከላከያ ሰራዊት 240 የእርድ ሰንጋና 107 በጎችና ፍየሎች ድጋፍ አድርጎል

  • Post comments:0 Comments

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 240 የእርድ ሰንጋና 107 በጎችና ፍየሎች ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ መንግስት ር/መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።ር/መስተዳድሩ እንደገለፁት መላው የክልሉ ህዝብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ የሞራል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ጁንታውና ዘራፊው የህወሓት ቡድን “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዲሉ እኔ ካልመራሁ ሀገር ይፍረስ የሚል ተራ እሳቤ በመያዝ ላለፉት 27 ዓመታት የፈፀሙትን ሀገርን የመዝረፍ ተግባር ለመድገም ፍላጎት ብኖራቸውም አልተሳካላቸውም በተባበረ የህዝቡ ትግል አልተሳካላቸውም ብለዋል።የክልላችን ህዝብ እስካሁን ካደረገው ድጋፍ በዘለለ በግንባሩ በአካል በመገኘት እስከማበረታታት ድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።የሲዳማ ክልል ህዝብ መንግስት ተገዶ የገባበትን ህግ የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፍና ከጀግናው መከላካያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆም ገልጸው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የክልሉ ህዝብ እስካሁን ላበረከተው አስተዋፅኦ ያላቸውን እክብሮትና አድናቆትም ጨምረው ገልፀዋል።የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

ምላሽ ይስጡ