በዘላለም ሲሳይ
ሕወሓት የውሸት ትርክቶችን በመፍጠር በሕዝቦች መካከል አለመተማመን እንዳይኖርና ግጭት እንዲፈጠር እንዲሁም ለብሄሮች ትምህክት ጠባብ የሚሉ የማሸማቀቂያ ታርጋዎችን በመለጠፍ ባለፉት 27 ዓመታት የሴራ ፓለቲካ ሲያራምድ ቆይቷል፡፡
የመከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ባለው የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ተግባር የሚወሰደን እርምጃ መቋቋም ያልቻለው የሕወሃት ጅንታ ቡድን ከመነሻውም እንደዓላማ አንግቦ የተነሳው የውሸት ፕሮፖጋንዳ ዛሬም በመከላከያ ሰራዊት እየተመዘገበ ያለውን አንጸባራቂ ድል በመካድ በየደቂቃው በቴሌቪዝን መስኮት ብቅ እያሉ አሸንፈናል፣ ጦር ደምስሰናል የሚሉ የማደናገሪያ ቃላትን እና የውጭ አገር ቅንብር ምስሎችን በመጠቀም ሕዝብን በተሳሳተ መረጃ በማደናር እንዲሁም ወጣቱን ወደ ጦርነት እንዲገባ ለማነሳሳት ሙከራ አድርገዋል፡፡ ሆኖም ግን እውነታው የተገላቢጦሽ ሆኖ በርካታ የትግራይ ሕዝብ የመከላከያ ሰራዊት እያካሄደ ባለው ተግባር ደስታቸውንና አጋርነታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ጅንታው ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ልክ ዓለማ ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ በግዳጅ ሕጻናትን በመመልመል ለጦርነት እንዲሰለፉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን የቡድኑን እኩይ ዓላማ የተረዱት በርካታ የጸጥታ ሃይሎች እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ወደ መቃብር እየሄደ ያለው የጥፋት ቡድን ባሰበው መልክ ሳይሆንለት ሲቀር የሃይማኖት ተቋማትን ፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ፣መሰረት ልማቶችን ላይ ያነጣጠሩ የጥፋት ድግሶችን በማዘጋጀት የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ደፋ ቀና እያለ ቢሆን ሁኔታውን የተረዳው የመከላከያ ሰራዊት የጅንታውን ጥፋት ከሕዝብ በመነጠል በጥንቃቄ ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡
በትግራይ ህዝብ ስም እየማለና እየተገዘተ የራሱን ሀብትና ጥቅም ሲያስከብር የኖረው ጅንታ ከእያንያንዷ ደሃ እናት በተሰበሰብ ግብር የመቀሌን እና ሕዝቦቿን አድገት ከፍ የሚያደርጉ መሰረተ ልማቶችን በማውደም እውነተኛ ባንዳነቱን አረጋግጧል፡፡
በጣረሞት ላይ የሚገኘው ይህ ዘራፊ ቡድን የትግራይ ሕዝብ እንደመሸሸዲያ ለዓመታት በጭቆና ስርዓት እንድትኖሩ ያደረጋቸውን ጅንታ በማጋለጥ እኩልነትና ወንድማማችነት የሰፈነባት አገር ለመገንባት በሚደረገው ሂደት የበኩላችንን ሚና እንወጣ መልዕክታችን ነው፡፡