You are currently viewing የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› በሚል ሀገር አቀፍ የድጋፍ መርሐ-ግብር ላይ ድጋፋቸዉን ገለጹ።

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› በሚል ሀገር አቀፍ የድጋፍ መርሐ-ግብር ላይ ድጋፋቸዉን ገለጹ።

  • Post comments:0 Comments

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተለያዩ የሥራ ክፍል ሓላፊዎችና አጠቃላይ ሠራተኛዉ በጋራ በመሆን ‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› በሚል ለሀገራዊ ጥሪ በከፍተኛ ተነሳሽነት ድጋፋቸዉን ገልጸዋል።ከፍተኛ አመራሩና ሠራተኛዉ ማክሰኞ፣ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ልክ ከረፋዱ 5፡30 ጀምሮ በያለበት በመቆም ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጃቸዉን በደረት ላይ በማድረግና ለአንድ ደቂቃ ደግሞ በማጨብጨብ ለሀገራችን ሰላምና ልማት ዘብ ለሆነው ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፋቸዉንና አክብሮታቸዉን ገልጸዋል፡፡ አመራሩና ሠራተኛዉም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለፈጸመዉና እየፈፀመ ላለዉ ገድልና ድሎች ስሜታቸዉን ለመግልፅ ይህን አጋጣሚ ያመቻቹ የኪነጥበብ ባለሙያዎችንና የሚመለከታቸዉ አካላትን አመስግነዉ ዕድሉ በመፈጠሩ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

ምላሽ ይስጡ