You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ የተሳተፈበት የቻይናና የአፍሪካ አገራት ገዥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢንተርኔት ውይይት አካሄዱ

ብልጽግና ፓርቲ የተሳተፈበት የቻይናና የአፍሪካ አገራት ገዥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢንተርኔት ውይይት አካሄዱ

  • Post comments:0 Comments

በቻይና የኮሚኒስት ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደው የቻይና አፍሪካ ገዥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከ25 በላይ የአፍሪካ አገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ውይይት ነበር ።በውይይቱ የቻይናና የአፍሪካ አገራት ግንኙነት በቀጣይ ተጠናክሮ ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ምክክር ተደርጎበታል፡፡ የአፍሪካ አገራት ፖለቲካ ፓርቲዎች ከቻይና ጋር በነበራቸው ግንኙነት መጠቀማቸውንና ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈለጉና ከቻይና ስኬት ብዙ የምንማረው በርካታ ጉዳዮች አለ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲም ጋር ያለውን ግንኙነት በቀጣይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጾአል፡፡ቻይና በባለፉት ሁለት አስርት አመታት ከፍተኛ የሚባል ስኬት ማስመዝገቧ ተግልጾል፡፡ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስተር ሶንግ ታው እንደገለጹት ቻይና በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መሪነት ለባለፉት አመታት በተለያዩ ዘርፎች ተዓምራዊ ሊባሉ የሚችሉ ስኬቶችን ማስመዝገቧን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በድህነት ቅነሳ ፣በሳይንስና ቴክኖሎጅ በመሰረተ-ልማትና በሌሎች የተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ 700 ሚሊዮን የቻይና ህዝብን ከድህነት አረንቋ ማላቀቃቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡የአፍሪካ አገራት ከቻይና ስኬት መማር አለባቸው ሲሉ የገለጹት ሚኒስተሩ በቀጣይ የአፍሪካ አገራት ለሚያከናወኑት የድሀነት ቅነሳና ሌሎች ስራዎች ላይ የቻይና መንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው አረጋግጠዋል፡፡በውይይቱ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የቀጣይ አምስት አመታት እቅድ ለተሳታፊዎቹ ተዋውቋል፡፡ ከአፍሪካ አገራት ጋር በጋራ ስለሚከናወኗቸው ጉዳዮችም ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል፡፡በአለም ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአፍሪካ አገራትም ይህ ወረርሽኝ ሲከሰት የአፍሪካ አገራትን ለመረዳት ቻይና ያደረገቸውን አስተዋጾ ከፍተኛ እንደነበር የውይይት ተሳታፊዎቹ አንስተዋል፡፡ በዚህ ረገድ በተለይ ኢትዮጵያ ከቻይና ለአፍሪካ አገራት የተደረገውን የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶችን ለየአገራቱ በማከፋፈል ረገድ ላደረገቸው አስተዋጾ የውይይቱ ተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ