ድርድርን በሚመለከት…

ጦርነት እንደ ወንፊት ነው። በዚያ ውስጥ ስንሽከረከር ያሰብነውን ማሳካት አንችልም። ሰላምና ብልጽግናን ለማስቀጠል ሲባል ጦርነትን ማስቀረት ያስፈልጋል። እየቀጠለ ከሄደ እንደ ሀገር እንደቅቃለን። ጦርነት ማቆምን ቀዳሚ ምርጫ ያደረግነው ለሰላማችን እና ለብልጽግናችን ስንል ነው። የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም፣ እያሸነፍክም ቢሆን ጦርነት መጥፎ ነው። ሰው ትገድላለህ፣ ዶላር ትተፋለህ። ሁሌም ሰላም ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን ሕልውና፣…

የዋጋ ግሽበት የማክሮ…

 ሀገራችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ሸቀጦች ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሕጋዊ መንገድ ታወጣለች። በዚያም ከ6000 በላይ ሸቀጦች ይገባሉ። ከነዚህ ውስጥ እገዳ የተጣለው በ39ቱ ሸቀጦች ላይ ብቻ ነው።  ለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ1 ቢሊየን ዶላር የሚበልጥ ወጥቷል፣ ይህም ለማዳበሪያ ካወጣነው እኩል ነው። ውሳኔው የተወሰነው ለሀገር ውስጥ ምርት ዕድል ለመስጠት፣ ለጥቁር ገበያ የተጋለጡ ሸቀጦች…

የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ…

 የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ ፈተና ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግር ነው። ባለፉት አራት ወራት የግሽበት ሁኔታ እየቀነሰ ነው። ይህም በተወሰዱ ርምጃዎች የተነሳ የተገኘ ነው። በበዓል ወቅት የሥጋ፣ የዶሮና የዕንቁላል ፍላጎት እንደሚያሻቅብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች እንዳይጎዱ ለማድረግ ሥራዎች ተሰርተዋል።  ከ9.5 ሚሊየን የሚበልጡ ተማሪዎች በቀን ሁለቴ የምገባ አገልግሎት ያገኛሉ። አሁን ከ200,000…

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ…

የመሬት አቅርቦት፣ ቀልጣፋ አሰራር (አውቶሜሽንን ማስፋት)፣ ብድርን በተመለከተ መንግስት እርምት የሚያደርግባቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። መሬት የህዝብም የመንግስትም ሳይሆን የሕገወጥ ደላሎች እና የዘራፊ ሹመኞች ነው። ይህንን በስር ነቀል ለውጥ መቀየር ያስፈልጋል። ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ስለ ሆነ፣ በአካታች ሀገራዊ ምክክር ከሚፈቱ ጉዳዮች አንዱ ነው። ቢያንስ በከተሞች መሬት የግለሰብ መሆን አለበት። በሕገወጦች ተግባር የተነሳ በርካታ ስራዎች እንደተፈለጉት ሊሰሩ…

ሸኔን በሚመለከት…

 ሸኔን በሚመለከት በሽብር መንገድ ዘላቂ ሰላም ማምጣት አይቻልም፤የወለጋ ሸኔና የሸዋ ሸኔ በሚል እርስ በእርሳቸው እየተዋጉ ይገኛሉ፤  የጦር መሳሪያ ታጥቆ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም፤ምንጊዜም ሰላምን ማረጋገጥ የሚቻለው በውይይት እና በንግግር ብቻ ነው፤  በሽብር የሚገኝ ነጻነት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲ የለም። የሸዋና የወለጋ ሸኔ እያለ እርስ በርሱ ሲዋጋ የሚውል ማእከላዊ እዝ የሌለው ሀይል ነው። ለኦሮሞ ሕዝብ…

መደመር የመከፋፈልን…

መደመር የመከፋፈልን ግንብ አፍርሶ፤ ዘረኝነትና ጎጠኝነትን ያስወግዳል፡፡ መደመር አንድነት የሚነግስበት ሰው በሰውነቱ ብቻ ክብሩና ነጻነቱ ተጠብቆ እንዲኖር እድል ይፈጥራል፡፡ መደመር የሚፈነጥቀው የወንድማማችነት ጮራ ትውልድ ተሻጋሪ ነው፡፡ ምክነያቱ ደግሞ መደመር ትብብር፣ መተጋገዝ፣ መደጋገፍን የሚያበረታታ በዛሬ መሰረት ነገን ማነጽ የሚያስችል እሳቤ በመሆኑ ነው፡፡ የመደመር እሳቤ ከዴሞክራሲ ስርዓት አንጻር ክፍተቶችን አርሞ የመግባባት ዴሞክራሲን በተሻለ መሰረት ላይ…