ኢ ት ዮ ጵ ያ በቅርብ ቀን ከጫፍ ጫፍ የሰላም አየር ይነፍስባታል፤ ህዝቦቿ በነጻነት የትም ሄደው መኖር ይጀምራሉ

ሰራዊታችን በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተጣለበትን ህዝባዊ አደራና በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተሰጠው ትዕዛዝ  መሰረት በመቀሌ የመሸገውን ዘራፊውን የህወኃት ቡድን ለህግ የማቅረብና ህግ የማስከበር ስራ በውጤታማነት እንደሚፈጽመው ጥርጥር የለውም፡፡ ሰሜናዊቷ ኮከብ መቀሌ የኢትዮጵያዊያን መዳረሻ ከተማ ናት፤ሁሉም የሚናፍቃት የታታሪ ህዝቦች ምደር፡፡ስለሆነም እየተወሰደ ያለው ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ግቡን ይመታ ዘንድ በከተማዋ የምትኖሩ ነዋሪዎች…

አገራችን ውስጥ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከህወሃት አጥፊ ቡድንና በጥምረት ከሚንቀሳቀሱት ኦነግ ሸኔና ካደራጇቸው የጥፋት ኃይሎች ውጭ የአገራችንን ሰላም ለማወክ የሚራወጥ ኃይል እንደሌለ ግልጽ ነው። ባለፉት ዓመታት ከባዕዳን ጋር ሳይቀር በማበር አገር ለመውጋት ሲያሴሩ የነበሩት እነዚህ ሃይሎች አሁንም ብዙሃኑ የአገራችን ህዝብ ሰላሙ እንዲመለስት ዘወትር የሚተጋውን ያህል የጥፋት ቡድኖቹ የየእለት ተግባራቸው በሰውና በንብረት ላይ ጥፋት ማድረስ…

ነገሮችን በትዕግስትና በሆደ ሰፊ የሚመለከተው መንግስት ሁሌም ቢሆን ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ጉዳዮችን በጥንቃቄ ለመያዝ ጥረት ሲያደረግ መቆየቱ በአደባባይ ያስመሰገነው ተግባሩ ነው፡፡ ይህ የህወሓት አጥፊ ቡድን ሀገርን ለማተራመስ ካለው የጠበቀ ፍላጎት አኳያ እና ይህንን ለማድረግ ያግዘኛል ያለውን እብሪት የተሞላበት ድርጊት ፈጽሟል፡፡ ባለው ጥቅምት 24 አመሻሽ ላይ የአገራችንንና የአህጉራችን ኩራት የሆነው የመከላከያ ኃይላችን ላይ ተኩስ በመክፈት…

ዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ጽንፈኛ ቡድኖች እንኳ የህወኃትን ያህል በገዛ ሀገራቸው ላይ የጥፋት ብትራቸውን ሲያደርሱ አይስተዋልም፡፡ሀገር ሀገር ነው፤ህዝብም ህዝብ፡፡የውስጥ ቄራኔያቸውን በህግ አግባብ መፍትሔ ያበጁለታል እንጂ ከዜጎች ግብር ተሰብስቦ የተሰሩትን መሰረተ ልማቶችና ተቋማት ላይ ጉዳት አያደርሱም፡፡ መንግስት ይሄዳል፣መንግስት ይመጣል፤ሀገር ግን ትቀጥላለች፡፡የህዝብ መገልገያ የሆኑትን ተቋማትንና መሰረተ ልማት ላይ በግዴለሽነት የበቀል እርምጃ መውሰድ ግን መቼም ይቅር…

የምንገኘው ኮር አመራርና ኮር ሃሳብ ወሳኝ በሆነበት ጊዜ ላይ ነው

የአማራ ክልል በሁሉም መንገድ ፈተና ውስጥ በሆነበት በዚህ ጊዜ ከመቸውም ጊዜ በላይ የሚያስፈልገው ኮር አመራርና ኮር ሃሳብ ነው። በየመድረኩ ያጋጠመንን ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ወሳኝ መድረክ በአሸናፊነት የምንወጣው በህዝባችን የቆየ ብልሀትና የአደጋ ጊዜ መሻገርያ አስተዳደራዊ ጥበብ ነው። የአማራ ክልል ህዝብ አንድነት የሚረጋገጠው ወሳኝ በሆነ መድረክ ላይ መሆኑ ዛሬን ጨምሮ የትላንት ፈታኝ አጋጣሚዎች ዋቢ ምስክር ናቸው።…

መንግስት ከወንጀለኞች ጋር ድርድር አይቀመጥም!

መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመቀልበስ የሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡የአገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬም በድል ታጅቦ ህግ የማስከበር ስራውን ቀጥሏል፡፡ ይህን እርምጃ ወደኋላ ለመቀልበስ በየአቅጣጫው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከመንዛት ጀምሮ አቅጣጫ የሚያሰቀይር እኩይ ተግባር መፈጸም የመንግስትን አቅም ያጠነክረው ይሆናል እንጂ ወደኋላ የሚመልሰው አይሆንም፡፡መንግስት በትግራይ የመሸገውን የጥፋት ቡድን ለፈጸመው…