የመልሚያ አቅሞቻችንን መለየት…

የመልሚያ አቅሞቻችንን መለየት፣ መገንዘብና ማልማት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለመጎናፀፍ ዓይነተኛ አማራጭ ነዉ። ሁሉንም ሀብቶቻችንን በማልማት የኢኮኖሚ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ ጀምረናል ። አምና የተጀመረው በበጋ መስኖ ስንዴን የማልማት ተግባር ዘንድሮም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሌማት ትሩፋት ንቅናቄው የእንስሳት እና የእንስሳት ተዋፅኦዎችን ፣ ወተት ፣ ዶሮ፣ ዓሳና ንብ የማነቡን ተግባር በወሳኝ መልኩ ዉጤታማ የማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የየአካባቢዎቻችንን ፀጋዎች ጥረን ግረን…

ብልጽግና የሚከተለው አቅጣጫ…

ብልጽግና የሚከተለው የዴሞክራሲ አቅጣጫ በትብብርና ውድድር ላይ የተመሰረተ፤ለብዝሃነትና ለህብረ ብሔራዊነት የተለዬ ቦታ የሚሰጥ፣የመግባባት ዴሞክራሲ ነው፡፡በህገ መንግስታችን ላይ የተመለከተውን እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትና ህብረ- ብሔራዊ ፌዴራሊዝም የመገንባት ዓላማ አለው፡፡ ብልጽግና የሚከተለው የኢኮኖሚ አቅጣጫ በኢኮኖሚ ረገድ ብልጽግና የሚከተለው እሳቤ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ፣የመንግስትን ጣልቃ ገብነት የሚፈቅድ፣አካታች ካፒታሊዝም…

የት እንደመር (Platform)

በመደመር የእመርታዊ ለውጥ ሀሳብ ውስጥ አንዱ የተደማሪዎች ፈተናና መደናገር ሊሆን የሚችለው ምኑ ላይ ወይም ከማን ጋር ነው የምደመረው የሚለው ሊሆን ይችላል። እራስን አጽድቆና አትልቆ ሌላውን ደግሞ አኮስሶና አዋድቆ የማየት ችግር ስላለብን ነው። ለራሳችን ካለን በጎነትና መልካም እይታ ቀንሰን ለሌሎች በመስጠት፣ በሌሎች ላይ ካለን አብጥልጥሎና አብጠርጥሮ የመፈተሽ ልምድ ደግሞ ቀንሰን በራሳችን ላይ ብንተገብረው ከማንም ጋር ለመደመር…

ብልፅግና ሀገር ማሻገር የሚችል…

ብልፅግና ሀገር ማሻገር የሚችል፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለለውጥ ዳተኛ ያልሆነ፣ መሻሻል የሚችል፣ የዴሞክራሲ መርሆችን ያልገፋ እና በተደማሪነት አቅም የሚያምን የሀሳቦች ባለፀጋ ነው፡፡ በብልፅግና ውስጥ የተሳባሰበው አመራርም በክህሎት፣ በለውጥ አቅም፣ በመደመር እሳቤ፣ ከመንደር እይታ ወጣ ባለ ሀገራዊ አስተሳሰብ የዳበረ እና አሁናዊ ለሆነው የለውጥ እንቅስቃሴ አቅም ሊሆን ይገባል፡፡ በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ከግብ ማድረስ የሚቻለው የተቋም (institution) እሳቤ…

ብልጽግና ህብረ ብሔራዊ አንድነትንና…

ብልጽግና ህብረ ብሔራዊ አንድነትንና ብዝኃነትን እንደ ጸጋ የሚመለከት ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና የሚሰጥ ፓርቲ ነው፡፡ ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ማንነታችን እርስ በርሱ የተጣመደ፣ የተሳሰረ እና የተዋሐደ መሆኑን በመገንዘብ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን በመቆም፣ አብረን በመሥራት፣ በመደጋገፍ እና በመተጋገዝ ብቻ እንደሚሳካ የሚያስገነዝብና የሚያምን ፓርቲ ነው። ህብረ ብሔራዊ አንድነት ታሪካዊና ነባራዊ በደሎችን ከማድበስበስ ይልቅ ታርመው እንዲሄዱ፣ ይህም…

የምንደመረው ነገን በጋራ ለማነጽ…

የምንደመረው ነገን በጋራ ለማነጽ፣ እንግዶቻችንን በፍቅር ለመቀበልና ለማስተናገድ፣ ደካማውን ለማገዝ፣ ያለንን ለማካፈል፣ ተግተን ለመስራት፣ የበደሉንን ይቅር ለማለት፣ በፍቅር ሁሉን ለማሸነፍ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን ከመበላላት መረዳዳት፤ ከመገፋፋት መተቃቀፍ እንዲሆንልን ነው። • በመደመር ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን እንሰራለን። ሳንደመር ስንቀር ኪሳራው ብዙ ነው። • መልካችን፣ ፍቅራችን፣ ደግነታችን፣ ጀግንነታችንም አንድ ዓይነት ነው። ነገር ግን የእኛ መደመር ለሌሎች አፍሪካ…