You are currently viewing ጠ/ሚ ዐቢይ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

  • Post comments:0 Comments

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮካ ኮላ ሊቀ መንበር ጄምስ ኩይንሲ እና የኮካ ኮላ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃኩዬስ ቨርሚዩለን ጋር ነው የተወያዩት።

በውይይታቸው ወቅትም ኮካ ኮላ በመጭው ክረምት በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ለታቀደው የ5 ቢሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማድረግ ቃል መግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና በአዲስ አበባ እየተተገበሩ ላሉ ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

ምላሽ ይስጡ