የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ለክልሉ ፓርቲ ጽህፈት ቤት፣ ለዞንና ለልዩ ወረዳ የፓርቲ የስራ ሃላፊዎች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ መላው የክልሉ አመራርና አባል የብልጽግና ፓርቲ የስነ-ምግባር ደንቦችንና ህጎችን ጠንቅቀው በማወቅ የፓርቲው ዓላማዎች እንዲሳኩ መስራት ይገባዋል ብለዋል።
ስልጠናው ከፌደራል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅርና አባል ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸው ስልጠናው በጥብቅ የፓርቲ ዲስፕሊንና ስክነት እንዲፈጸምም መመሪያ አስተላልፈዋል።
ስልጠናው አመራሩና አባሉ ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር መርሆዎችንና ህጎችን ጠንቅቀው እንዲያውቁና በዕለት ተዕለት ተግባራቸው እንዲጠብቋቸው እንደሚያደርግም ዶክተር ዲላሞ አስታውቀዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል ስልጠናው የፓርቲ ጤናማነቱ የተረጋገጠ አመራርና አባል ለመፍጠርና ለመገንባት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
መሰል ስልጠናዎች እስከታችኛው መዋቅር ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት ሃላፊው ስልጠናዎቹ አመራሩና አባሉ የስነ-ምግባር ጥሰቶችና ሊወሰዱ የሚችሉ የእርምት እርምጃዎችን በቅጡ እንዲገነዘቡ ያስችላሉ ብለዋል።
በተከታታይ በሚሰጡት ስልጠናዎች አመራሩና አባሉ ስለፓርቲው ስነ -ምግባሮችና ህጎች የተሻለ መረዳት እንዲያገኝና አውቆ ለማሳወቅ እንዲችል ሰፊ እድል እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።
አመራሩና አባሉ በተሻለ ደረጃ መብትና ግዴታውን አውቆ እንዲሄድ ለማድረግና መብቱን ለማስከበር ስልጠናው ትልቅ እገዛ እንዳለውም አቶ አብዱልዋሪስ አስታውቀው አባላትና አመራሩ ባለማወቅ ወደስህተት እንዳይገቡ በማድረግም ሚናው የላቀ ነው።
የብልጽግና ፓርቲን የስነ-ምግባር መርሆዎችና ህጎችን በአመራሩና በአባሉ ውስጥ ለማስረጽም በቀጣይ በዞኖች፣በልዩ ወረዳዎች፣በወረዳዎች፣
ለመሰረታዊ ድርጅትና ለህዋሳት አመራሮችና በአጠቃላይ ለፓርቲው አባላት በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰጥም አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ
“ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!”