You are currently viewing የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

  • Post comments:0 Comments
የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ እና በሁሉም አካባቢዎች በኢንስፔክሽን ለማረጋገጥ በተከናወኑ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን በማስመልከት ውይይት ተካሂዷል።
የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ዳንኤል ካሳ የውይይት መድረኩን በማስመልከት እንደገለጹት የዘርፉ ዋነኛ ዓላማ የውስጠ ፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም እና የፓርቲ አሰራሮች ተጠብቀው እንዲከወኑ ማስቻል መሆኑን በማንሳት ከዚህ አንፃር በኮሚሽኑ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በጥንካሬ እና በጉድለት እንደሚገመገሙ እንስተዋል።
አቶ ዳንኤል አክለው እንዳነሱት ኮሚሽኑ የውስጠ-ፓርቲ ስራዎች በአሰራራቸው መሰረት በአመራሩና በአባሉ ዘንድ እየተተገበሩ ስለመሆናው በተጨባጭ የማረጋገጥ ስራ የሚሰራ ተቋም ነው በማለት ከዚህ እንፃር በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ይህንን ከማረጋገጥ አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በድጋፍ እና ክትትል መመልከት መቻሉን ገልጸዋል ።
በውይይት መድረኩም ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ዳንኤል ካሳ ፣ የክልሉ የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት መኮንን እና የኮሚሽን ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሁሉም ወረዳዎች የዘርፉ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
ምንጭ:- የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ቅ/ጽ/ቤት
“ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!”

ምላሽ ይስጡ