You are currently viewing የ5ኛው የጋራ ምክክር መድረክ ተሳታፊዎች የጉብኝት መርሐግብር አካሄደዋል::

የ5ኛው የጋራ ምክክር መድረክ ተሳታፊዎች የጉብኝት መርሐግብር አካሄደዋል::

  • Post comments:0 Comments
በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተካሄደው የኮሚሽናችን የጋራ ምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በጅግጅጋ ከተማ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን፣ አዲሱን በቅርቡ የሚመረቀውን ለአገልግሎት ክፍት የክልሉን ም/ቤት ዘመናዊ ህንፃ፣ ግንባታው በመገባደድ ላይ የሚገኘውን የሶማሊ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንጻ ስራዎችን በመጎብኘት እንዲሁም ፋፈን ዞን ሸበሌይ ወረዳ የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ቅ/ ጽ/ቤት ጉብኝት እና ከቀበሌዎችና ወረዳው የኮሚሽን አባላት ጋር ውይይት ከተደረጋ በኃላ የችግኝ መትከል መርሀ ግብር ተካሄዷል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የኮሚሽኑ ም/ሰብሳቢ ዶክተር ደስታ ተስፋው ወደ ሶማሊ ክልል በመምጣት የምክክር ኮሚሽኑን መድረክ ለማካሄድ የተወሰነው በዘፈቀደ የተወሰነ አለመሆኑን ጠቅሰው በክልሉ እየተካሄደ ያለው የኮሚሽኑ ስራ እንቅስቃሴ አበረታች በመሆኑ የመድረኩ ታዳሚዎች ልምድ እንዲወስዱ ለማስቻል ነው ብለዋል።
በመጨረሻም የክልሉ መንግስት፣ የኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የሸበሌ ወረዳ ህዝብ ላደረገልን ደማቅ መስተንግዶ አመስግነዋል።
የኮሚሽኑ ጸሐፊ የሆኑት ዶክተር ሁሴን ቃስም በበኩላቸው 5ኛው የጋራ ምክክር መድረክ በክልላችን በመደረጉ እጅግ በጣም ደስተኞች ነን ብለዋል።
ክልሉ ለውጡን ተከትሎ በበርካታ አገራዊና ክልላዊ የልማት አጀንዳዎች በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በክልሉ አሁን እየታየ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ በአገራችን ብሎም በሶማሌ ክልል በአጭር ጊዜ ብልጽግና እንደሚረጋገጥ ያመለክታል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
“ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!”

ምላሽ ይስጡ