You are currently viewing የመተሳሰብና የአብሮነት እሴታችን የዘመናት ሂደት ውጤት ሆኖ ወደዚህ ትውልድ መድረስ ችሏል፡፡

የመተሳሰብና የአብሮነት እሴታችን የዘመናት ሂደት ውጤት ሆኖ ወደዚህ ትውልድ መድረስ ችሏል፡፡

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ የህዝቦችና የዜጎች የመቻቻል፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት ሆና ለዘመናት ጠብቃ የቆየች ሀገር ናት፡፡ ይህ የመቻቻልና
የአብሮነት ባህል በተለይ በተለያዩ ሃይማኖቶች ግንኙነት ጎልቶ የታየ ከመሆኑ አንጻር በዚህ ረገድ አገራችን በብዙ ሀገሮች ዘንድ
በምሳሌነት እንድትጠራ አድርጓታል፡፡
የመተሳሰብና የአብሮነት እሴታችን የዘመናት ሂደት ውጤት ሆኖ ወደዚህ ትውልድ መድረስ ችሏል፡፡ ይኸውም መሠረታዊ
ባህርይ ሆኖ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በቅብብል የመጣ የመቻቻል ባህል ነው፡፡በተለያዩ እምነት ተከታዮች በሰላም አብሮ መኖርን
አስመልክቶ ሁሉም አወንታዊ የሆነ አመለካከት አላቸው፡፡
ይኸውም በተለይ የአይሁድ፣ የክርስትናና እስልምና የሰው ልጅ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ ክቡር ነው የሚል እምነት
አላቸው፤ ሁሉም ሰው በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ስለሆነም እኩል ነው፡፡ለሁሉም እምነቶች፣ባህሎች እና እሴቶች ተገቢውን
ክብርና ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡
አንደኛው አካባቢ የሚጠቀምበትን እሴት በሌላው አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ እንደራሱ አይቶና ጠብቆ ማክበርና እንዲከበሩ
ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ይህን ማድረግ ስንችል እያንዳንዳችን የምንጠቀምባቸውን እና የምናከበራቸውን እሴቶቻችንን እንዲከበሩ
ማድረግ የሚቻለው፡፡ የእኛ እና የእነሱ የሚባል እሴት የለም ሊኖርም አይችልም፡፡
በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች በሚከበሩ ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላት ለምሳሌ መስቀል፣መውሊድ ፣ጥምቀት፣
ኢድ አል ፈጥር፣ኢሬቻ፣የሲዳማ ክልል የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ፣ያ ሆዴ መስቀላ እና ዮ-ማስቃላ የጋሞ
ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ፣የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ”፣ …እና በመሳሰሉት አገራዊ እሴቶቻችን ሁሉም
በሰላም ተጀምሮ በፍቅር ይጠናቀቅ ዘንድ ፍላጎታቸው ነው፡፡ለዚህም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልዩ ልዩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ
በዓላት ሲከበሩ ምንም አይነት ኮሽታ ሳይሰማባቸው በሰላም እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን የማስተባበሩን
ሚና እየተወጡ የሚገኙት፡፡
በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወጣቶችና ሌሎች ምዕመናን
ከበዓሉ አስተባባሪ ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን በማስተባበር ሀላፊነታቸው ሲወጡ እናያለን፤የኢድና መውሊድ የመሳሰሉ
በዓላት ሲከበሩም ቢሆን የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፊት ሆነው
የማስተባበሩን ሚና ሲወጡ ማስታዋል ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን አዲስ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የሃይማኖትን ብዝሃነትን
በማስተናገድ የዘመናት ታሪክ ላላት ኢትዮጵያ አብሮ የመኖር ባህላችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ዕሙን ነው።
ሁላችንም የየራሳችን የምንከተለው ዕምነትና ሀይማኖት ይኖረናል፤ሁሉም ዕምነቶቻችን ደግሞ ሰላም ፣ፍቅርን ፣መቻቻልንና
እርስ በእርስ መከባበርን አጥብቀው ያስተምራሉ፡፡ለዚህም ነው ሁሉም ሀይማኖቶች ለሰላም ያላቸው ሚና የጎላ ነው የሚባለው፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ለእሴቶቻችን ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ በተደጋጋሚ ለህዝብ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ስለሆነም
ሁሉም እሴቶቻችን በእኩል ደረጃ ተገቢውን ክብር እንዲያገኙ እና የትኛውንም እሴት ሊሸረሽሩ የሚችሉ ሁኔታዎች
በተገቢው መንገድ መጠበቅ እንዳለበት ያምናል::

Leave a Reply