You are currently viewing አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤም ኤፍ ባወጣው የ2023 የኢኮኖሚ ምጣኔያዊ ሪፖርት መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤም ኤፍ ባወጣው የ2023 የኢኮኖሚ ምጣኔያዊ ሪፖርት መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

  • Post comments:0 Comments
አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤም ኤፍ ባወጣው የ2023 የኢኮኖሚ ምጣኔያዊ ሪፖርት መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
የሀገራችን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 156.08 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ በዚህም ከአለም ሀገራት 59ኛ ደረጃ መቀመጥ ችላለች፡፡
እንደ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ባለፉት አመታት ውስጥ በከባድ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች እየተፈተነች ቢሆን
ታላላቅ ድሎችን የማስመዝገብ ጉዟችንን አጠናክረን ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየንበት ጊዜ ነው።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከድህረ ጦርነት በኋላ ሊያጋጥማት የሚችሉ መንኮታኮቶችን ቀድመን በመረዳት በጦርነት ወቅትም ቢሆን ስንዴን ለውጪ ገበያ
ኤክስፖርት ለማድረግ ይፋ ያደረግነው እቅድ ከፍተኛ ፍሬ አፍርቶ ለኢኮኖሚ እድገታችን ግብአት መሆን ችሏል።
በቡና፣በቀንድ ከብቶች፣በጥራጥሬ እና በቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ የፈጠርነው የግብርና አብዮት በግብርናው ዘርፍ ላይ በተግባር
ላይ ከዋለው የሪፎርም ስራዎች ጋር ተዳምሮ አሁን ላይ የተገኘው ውጤት አመርቂ እንዲሆን አስችሎታል።
ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን በመፍጠር የሌማት ትሩፋት እና አረንጓዴ አሻራን የመሰሉ ሀገር አቀፍ የልማት ንቅናቄዎችን በመፍጠር ምርታማነትን በከፍተኛ
ሁኔታ ማሳደግ እንዲቻል ከራስ አልፎ የውጪ ገበያ ሊቀርብ የሚችል የኢኮኖሚ ግብአት መጓደል እንዳይኖር ሰፊ ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል።በርካታ ውጤቶችም ተመዝግበዋል።
እንደ ሀገር ያስመዘገብነው የምጣኔ ሀብት ደረጃ በጎ ሆኖ ሳለ በቀጣይ የኑሮ ውድነትን የመሰሉ ፈተናዎች አኮኖሚያችን ላይ ጥቁር ጠባሳ እንዳይጥሉ
በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ በዜጎች ዘንድ ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የኢኮኖሚ ስርአት ማስመዝገብ እንደሚገባን ፓርቲያችን ብልፅግና በጥብቅ ያምናል።
በቀጣይም የኑሮ ውድነትንና የስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ ሌሎች አንገብጋቢ የሆኑ ችግሮችን ከሕዝባችን ጋር በመሆን ለመፍታት የተጠናከረ ስራ መስራታችንን ይቀጥላል።
በተጨማሪም በማእድን ፣በኢንዱስትሪው፣በማኒዩፋክቸሪንግ ዘርፍ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርአት
ለመገንባት ከመላው ህዝባችን እና ወዳጅ ሀገራት ጋር በትብብር የምንንቀሳቀስ ይሆናል።
እንደ ሀገርም የኢኮኖሚ እድገት ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ የፀጥታ መደፍረስ የሰላም ሁኔታ ላይ አሁን በጀመርነው ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እየፈታን በመሄድ ተጨማሪ
ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን በመሳብ መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማድረግ እና ለዜጎቻችን የስራ እድል በመፍጠር ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርአት የመገንባቱን ሂደት አጠናክረን እናስቀጥላለን።

ምላሽ ይስጡ