You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ

  • Post comments:0 Comments
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው የአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል።
ከዚህ በፊት ዳያስፖራውን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያነሳቸው የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሕግ ሪፎርሞችን ማከናወኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችንም በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ዳያስፖራውም እያደረገ ያለውን ሀገሩን የማገዝ ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳስበዋል።

ምላሽ ይስጡ