ብልጽግና ፓርቲ ብሔራዊ መግባባትን…

ብልጽግና ፓርቲ ብሔራዊ መግባባትን…

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና ፓርቲ ብሔራዊ መግባባትን ለማዳበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ በአገራችን የቂም እና የጥላቻ ታሪክ ምዕራፍ እንዲዘጋ ማድረግ ነው፡፡
ይህን ለማሳካት ባህላዊና ዘመናዊ የእርቀ ሰላም ግንባታ አማራጮችን በመጠቀም እርቀ ሰላምን ለማምጣት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው፡፡ለቀጣዩ ትውልድ ቂምና ቁርሾ ሳይሆን ሰላም እና ወንድማማችነትን ለማውረስ የእርቀ ሰላም አማራጮችን ሁሉ እየተጠቀመ ይገኛል፡፡
ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣትና እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሐሳብ መቀራረብ ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት ብሔራዊ መግባባት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ጥናት የሚያደርግ እና ሂደቱን የሚመራ ተቋም በማቋቋም በልዩ ትኩረት እየሰራበት ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ለአገረ መንግስት ቀጣይነት መሰረታዊ በሆኑ ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ሁሉንም የአገራችን ህዝቦች አካታች በሆነ መልኩ የውይይት አውድ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

Leave a Reply