ብልጽግና ፓርቲ በፈታኝ…

ብልጽግና ፓርቲ በፈታኝ…

  • Post comments:0 Comments

ብልጽግና ፓርቲ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ባለችው አገራችን ከየትኛውም ጽንፍ ሳይወግን ችግሮችን ተቋቁሞና መስዋዕት ከፍሎ ኢትዮጵያን ለማሻገር ቆርጦ የተነሳ  ነው፡፡

በኢትዮጵያ የነበረውን ኢፍትሃዊ ተሳታፊነትና አካታችነት የጎደለው አካሄድ በመለወጥ ሁሉም እኩል የሚሳተፍበትና የሚወከልበትን እድል መፍጠር የቻለ ፓርቲ ነው ብልጽግና፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል እውነተኛ ፌዴራሊዝም ለመትከል የሰራ፤ ሁሉም በፍትሃዊ መንገድ የሚወከልበትና አካታች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠርም በትጋት ተንቀሳቅሶ ውጤት ማምጣት ችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ያጋጠሙ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ የመጣው ብልጽግና ፈተናዎችን በድል ማለፍ የቻለው አካታችና ሁሉን አቀፍ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ በመሆኑ ነው፡፡

Leave a Reply