You are currently viewing በብልጽግና ዘመን የመጣውን…

በብልጽግና ዘመን የመጣውን…

  • Post comments:0 Comments
በብልጽግና ዘመን የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ ከዚህም በላይ በአግባቡ ለማጣጣም አስተዋይነትን ይፈልጋል፡፡ ሀገራችን በበርካታ ሀገራዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ውስጥ ነው ያለችው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ፈተናዎችን ተጋፍጠን አገራዊ ብልጽግናን መድረስ የምንችልው ከፓርቲያችን ጎን መሆን ስንችል ነው፡፡
በሀገር ውስጥም በህዝብ መካከል ሰላማዊ ግንኙነትና አንድነት እንዲጠናከር እና ኢትዮጵያ እንደ ብዝህነቷ ያካበተቻቸው የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህልና የአንድነት መንፈስ እንዳይሸረሸር እና ለለውጡ እንቅፋት ከሚሆኑ ነገሮች በመራቅ የጋራ ሰላማችንን ከመዳፋችን አጥብቀን ልንይዘውና ልንጠብቀው ይገባል፡፡
አገራዊ ለውጡ ሰላምን በጽኑ ይፈልጋል፤ሰላምን ማስጠበቅ ደግሞ ከእያንዳንዱ ሰው ይጠበቃል፤ ሰላም የሚመነጨው ከእያንዳንዱ ቤትና ግለሰብ እንጂ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ብቻ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡
ለውጡን በአግባቡ ለማጣጣም ሰላማችን በእጃችን መሆኑን ምንጊዜም ማስታወስ ተገቢ ነው፤ ይህ ሲሆን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሊገጥሙንን የጋራ ፈተናዎች በድል ተሻግረን ከብልጽግናው ማማ ላይ መድረሳችን ዕውን ይሆናል፡፡

ምላሽ ይስጡ