You are currently viewing ኢትዮጵያ የምትበለጽገው…

ኢትዮጵያ የምትበለጽገው…

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ የምትበለጽገው እኛ አገራችንን ለመለወጥ በፈለግንበት መጠንና የጋራ ራዕይ በሰነቅንበት ልክ ብቻ ነው፡፡ኢትዮጵያ ካዘመመችበት ቀና የምትልበት ጊዜው አሁን ነው፤ይህን ለማሳካት የዛሬ ህያው ኢትዮጵያዊያን ታላቅ አደራ ተጥሎብናል፡፡
ይህንን አደራ ጠብቀን የዘመናት በጎ ድምር ውጤቶችን አጎልብተን ኢትዮጵያ የተባለችውን መርከብ ሞተሯን አድሰን ማዕበል ወጀቡ ፈፅሞ እንዳያናውጣት እና እንድትጓዝ ማድረግ ደግሞ የየትውልዱ የኢትዮጵያ ልጆች አደራ ይሆናል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመታት ዴሞክራሲን በስርዓተ መንግስቷ ለመትከል ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጋለች፣ተስፋና ስጋት ዕድልና ፈተና እየተፈራረቁባት አያሌ ውጣ ውረዶችን ተሻግራ እዚህ ደርሳለች፡፡
የማንነት ከከተሜ እስከ ባለአገር ከመለዮ ለባሽ እስከ ምሁር፣ከወጣት እስከ ጎልማሳ፣ከልሂቅ እስከ ደቂቅ መላው የአገራችን ህዝቦች የተሳተፉበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት የዘመናት የህዝብ ጥያቄ ነበር፡፡
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

ምላሽ ይስጡ