You are currently viewing መደመር የማህበራዊ…

መደመር የማህበራዊ…

  • Post comments:0 Comments
መደመር የማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን ጨምሮ ሁሉንም ግላዊና ማህበረሰባዊ የህይወት ዘይቤን የሚነካ እሳቤ ነው፡፡አላማዎቹም አገራችን ኢትዮጵያ ልትሄድበትና ልትደርስበት የሚገቡ መንገዶችና መዳረሻዎች ናቸው፡፡
ለዕሳቤው መዳበር ገፊ ምክንያቶች በአገራችን ባለፉት ዓመታት የተቀጣጠለው አገራዊ ለውጥ ፍንትው አድርጎ ያሳየንና ዘላቂና አፋጣኝ መፍትሔ የሚፈልጉ አገራዊ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡
በመሆኑም የመደምር እሳቤ የአገራችንን ተጫባጭ ችግሮችና ህሊናዊ ሁኔታዎች መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የዕሳቤው ምንጭ አገራዊ ተጨባጭና አውዳዊ ሁኔታዎች በመሆናቸው ለመደመር የሚሰጠው ትርጓሜም ከዚሁ የሚመነጭ ነው፡፡
አለም አቀፍ ዕውቀቶች የመደመርን ሐሳብ ለማዳበር አጋዥ ሚና አበርክተዋል፡፡ሆኖም ግን የእነዚህ ዓለም አቀፍ ዕውቀቶች ፋይዳ መለኪያውና ማንጠሪያው ተጨባጭ ውስጣዊ አገራዊ ሁኔታ ነው፡፡
የመደመር ዋነኛ ዓላማ አገራችን ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበቻቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድሎች ጠብቆ ማስፋት፣የተሰሩ ስህተቶችን ማረም፣እንዲሁም የመጻኢውን ትውልድ ጥቅም እና ፍላጎት ማሳከት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ