ጦርነት እንደ ወንፊት ነው…

ጦርነት እንደ ወንፊት ነው…

  • Post comments:0 Comments
ጦርነት እንደ ወንፊት ነው። በዚያ ውስጥ ስንሽከረከር ያሰብነውን ማሳካት አንችልም።
ሰላምና ብልጽግናን ለመስቀጠል ሲባል ጦርነትን ማስቀረት ያስፈልጋል። እየቀጠለ ከሄደ እንደ ሀገር እንደቅቃለን።
ጦርነት ማቆምን ቀዳሚ ምርጫ ያደረግነው ለሰላማችን እና ለብልጽግናችን ስንል ነው። የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም፣ እያሸነፍክም ቢሆን ጦርነት መጥፎ ነው።
ሰው ትገድላለህ፣ ዶላር ትተፋለህ። ሁሌም ሰላም ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን ሕልውና፣ ልዕልና እና አንድነት የሚገዳደር ነገር ሲፈጠር፣ አንድነታችንን ልዕልናችንን ብሄራዊ ጥቅማችንን ሲነካ መፋለማችን አይቀርም።
እነዚህን ነገሮች ለማዳን ከተቻለ ድርድር መጥፎ አይደለም። ኢትዮጵያ ሰላም እድገትና አንድነት መሄድ የማንፈልግባቸው ቦታዎችም ቢሆን እንሄዳለን።
የትግራይ ሕዝብ የጦርነት ድምጽ መስማት ይብቃው ያልነው፣ ሽምግልና የላክነው ጦርነት ሳይጀመር በፊት ነው።
አምና ጦርነቱ ሰንሜ ሸዋ ደርሶ ዘምተን ድል ካደረግን በኋላ እስረኞች እንፍታ ስንል ስንት ወዳጆችና ደጋፊዎች ናቸው ያኮረፉን። ያንን በማድረግ ሰላምን ማጽናትን እውን ለማድረግ ከተቻለ መደረግ ነበረበት።
ሰላምን የምንፈልገው ከሰላም ማትረፍ ስለምንችል ነው። ኢትዮጵያ ከሰላም ታተርፋለች። እንደ ሀገር ሰላም ትርፋማ ነው። አንዳንዶች ይቃረናሉ ለተባለው፣ ሰላም የሚያስከፋቸው ሀይሎች የጦርነት ፈላጊዎች መሆናቸው መታወቅ አለበት።
ከጦርነት የሚያተርፉ የጦርነት ነጋዴ ሰዎች ሰላምን አይፈልጉም። ጦርነት የማይፈልጉ የሰላም አምባሳደሮች ደግሞ አሉ። ግራ የሚያጋቡት ሁለቱንም የማይፈል ጉናቸው። ውስጣቸው ያላረፈ ሰዎች ሰላምን አይፈልጉም። ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን የህግ መከበር ነው።
ሕግ እና ስርዓት በሀገራችን እንዲከበር የሚደረገው ማንኛውም ንግግር እና ድርድር የሚጎዳ አድርጌ አላየውም። ተወያይተናል ተስማምተናል ፈርመናል፣ የገባነውን ቃል እውን በማድረግ ቃላችንን መጠበቅ ያስፈልገናል። በሂደቱ ችግር እንዳያጋጥም አጥብቀን መስራት ይኖርብናል።

Leave a Reply