ህብረ-ብሔራዊነትን የተላበሰ የፌደራሊዝም ስርአትን ብልፅግና ለምን መረጠ?

ህብረ-ብሔራዊነትን የተላበሰ የፌደራሊዝም ስርአትን ብልፅግና ለምን መረጠ?

  • Post comments:0 Comments
1. ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ሀገር እንደመሆኗ መጠን የሁሉንም ብሄሮች የባህል፣ የቋንቋ፣ የእምነት፣ ዘይቤን በእኩልነት ለማክበር ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራሊዝም ስርዓት ተመራጭ ነው። በመካከላቸው የሚፈጠሩ ልዩነቶችን ለማቻቻል እና ልዩነቶችን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመፍታት አግባብነት ያለው የፖለቲካ መሳሪያ ነው፡፡
2. ዜጎችን በየአካባቢው ባለው ጉዳያቸው ላይ ሙሉ የስልጣን ባለቤት በማድረግ ምርጫቸውንና ፍላጎታቸውን ታሳቢ ያደረገ የሕግ ማዕቀፍና የእቅድ ባለቤት ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ የአካባቢ አስተዳደሮች የአካባቢውን ፀጋ መሰረት ያደረገ የአፈፃፀም አቅጣጫ እንዲከተሉ ሲያስችላቸው ነዋሪዎች ደግሞ መንግስት በአቅራቢያቸው እንዳለ፣ ጥያቄያቸው በአካባቢያቸው ባለው አስተዳደር እንደሚመለስ ስለሚረዱ ከመንግስት ጋር ያላቸው ቁርኝት የጠበቀ ይሆናል፡፡
3. አካባቢያዊ ጉዳዮችን በፍጥነትና ቅልጥፍና ከማስተዳደር በተጨማሪ ከማዕከላዊ መንግስቱ የሚወርዱ የተወሰኑ ክልል ተኮር ጉዳዮችንም በብቃት ለማስተላለፍና ለማስፈፀም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ይህ ደግሞ በፌዴራል መንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመንና መረዳዳት እንዲኖር ያግዛል፡፡
4. ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ልዩነትን ውበት የማድረግ ትልቅ ሀይል ያለው የመንግስት ስርአት መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ የጥቂቶች ሳትሆን የብዙዎች ድምር እንደመሆኗ ህብረ ብሔራዊ ቀለሟን አጉልቶ ለማሳየት በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳል።
5. እያንዳንዱ ዜጋ ያደገበትን እና የኖረበትን የኑሮ ስርዐት ሳይለቅ በባህሉና በወጉ ኮርቶ የሌሎችን አስተሳሰብ እና እምነት አክብሮ በእኔነት በመቆርቆር ኢትዮጵያ የኔ ናት የሚል ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ ያስችላል።
6. በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው በቋንቋ በባህል እና ተመሳሳይ የሆኑ ዜጎች ፍላጎታቸው ተጠብቆ በአንድ ላይ ተሰብስበው መኖር እንዲችሉ ማድረግ ያስችላል። እያንዳንዱ ብሄር የሀገሪቱ ክፍል አንድ አካል ሆኖ በመኖሩ ብቻ ማግኘት በሚገባው ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ላይ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርገዋል።
7. ሁሉም አካባቢዎች በዙሪያቸው ያለውን እምቅ ሀብት (Hidden treasure) አውጥተው ለሀገራችን ኢኮኖሚ አስተዋፆ ማበርከት እንዲችሉ እና የሀገራቸው ኢኮኖሚ ዋልታ እንዲሆኑ እድሉን ይከፍታል። በዚህ ሂደት አንድ አካባቢ የተፈፀመ መልካም ልምድ በሌሎቹ ክልሎችና በማዕከላዊ መንግስቱም ጭምር እንዲተገበር መነሻ ሊሆን ይችላል።
8. ዜጎች የእኩልነት መብታቸው ተከብሮ ወግ እና ልማዳቸውን ሳይለቁ የትምህርት፣ የመሰረተ ልማት፣ የሰላም ተጠቃሚ እንዲሆኑ እገዛ ያደርጋል።
9. ብሄር ተኮር የሆኑና ዘረኝነትንና ጎሰኝነትን መሰረት ያደረጉ ጥላቻ የተሞሉ አስተሳሰቦችን እንዲመክኑ በማድረግ ሁሉም ብሔር የራሱን ወዶ የሌሎችንም እንዲያከብር ብልፅግና ፓርቲ የሚከተለው ህብረ-ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርአት በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳል ።

Leave a Reply