ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ካስተላለፉት መልዕክት በጥቂቱ፡-
- ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች በመሬት ላይ ያስገኙትን ታሪካዊ ድል በደቡብ አፍሪካ በነበረው የሰላም ውይይት ዳግም የሚያስረግጥ የሰላም ድል ማግኘት ተችሏል፤
- በድርድሩ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሃሳብ 100 በመቶ ተቀባይነት አግኝቷል፤
- የዛሬ ሁለት ዓመት ባልተገባ መንገድ ከወንድሞቻችን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር፤ የኢትዮጵያ ልጆች በገዛ ወንድሞቻቸው ባልተገባ ሁኔታ በተኙበት ታርደው፣ ተገድለው፣ ተገፍተው ነበር፤
- በኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና አንድነት ለመጣ ሁሉ ግንባራችንን ለአረር ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ያሳየንበት ነበር፤
- ኢትዮጵያ የምትፈልገው ሰላምና ብልፅግና እንጂ ጦርነት አይደለም፤
- በደቡብ አፍሪካ በነበረው የሰላም ድርድር ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች በመሬት ላይ ያስገኙትን ታሪካዊ ድል ዳግም የሚያስረግጥ የሰላም ድል ማግኘት ተችሏል፤
- ከተገኙ ዋና ዋና ድሎች መካከል አንደኛው የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ለድርድር አይቀርብም፤
- ለኢትዮጵያ አንድነት የሞቱና የቆሰሉ ጀግኖች ራዕያቸውና ህልማቸው ዕውን ሆኗል፤
- በአንድ አገር መኖር ስለሚገባው የአገር መከላከያ ሠራዊት አስፈላጊነት ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል፤
- እንደ ጋሞ ባሉ አባቶች እግር ሥር ያደገ ሁሉ ነገር በንግግርና በውይይት እንደሚፈታ ያውቃል፤
- በአንድ አገር ውስጥ ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም በሚለው ጉዳይ ከስምምነት ላይ ተደርሷል
- ሕጋዊነትን ማስፈን ላይ በተደረገው ውይይትም ሕግ መከበር ይኖርበታል፤
#prosperity