You are currently viewing በጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመበት 2ኛ አመት ታስቦ ዋለ

በጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመበት 2ኛ አመት ታስቦ ዋለ

  • Post comments:0 Comments

በጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመበት 2ኛ አመት ታስቦ ዋለ

ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመበት ጥቃት 2ኛ አመት በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ታስቦ ውሏል፡፡

በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት በፓርቲው የስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ  ኢትዮጵያ  ዛሬም ድረስ በፅናት እንድትቆም መስዋዕትነት ለከፈሉ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ያሉ ሲሆን ይህን ቀን ለአገር አንድነት ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ የፀጥታና የደህንነት አባላት ሁሉ በክብር የሚወሱበት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘመናት ብሔራዊ ክብሯን ሉዓላዊነቷን ሳታስደፍር የኖረችው በየዘመኑ በኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት መሆኑን ያወሱት አቶ ሞገስ የሰላም ድርድሩ ውጤታማ በሆነ መልኩ በተጠናቀቀበት ማግስት ይህን ማክበራችን ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ጦርነት መጨረሻው እልቂት መፍጠር ነው ያሉት አቶ ሞገስ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ጦርነት በድርድር ምላሽ ባገኘበት ወቅት በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው ብለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ቀኑ የታወሰ ሲሆን ኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ቀኑ ታስቦ ውሏል፡፡

ምላሽ ይስጡ