ያለፉት አራትና አምስት…

ያለፉት አራትና አምስት…

  • Post comments:0 Comments
ያለፉት አራትና አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ተስፋና መከራ፣ አንድነትና ልዩነት፣ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትና ውግዘት፣ እመርታና ጉተታ፣ ነጻነትና ግጭት ያስተናገድንበት ጊዜ ነው ማለት ይቻላል።
ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆቿን ያገኘችበት ብቻ ሳይሆን ያጣችበትም ጊዜ ነው። ቀረ፣ ሊያበቃለት ነው የተባለው ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን፣ ሙሌቱ ተገባድዶ ኃይልን ማመንጨት ጀምሯል።
የድርቅና የጉስቁልና ምድር የተባለች ሀገር ቢልዮን ችግኞችን በመትከልና በየሥፍራው ፓርኮችን በማበጀት የምድረ ገነትነት ግስጋሤዋን ቀጥላለች። የህልውናዋ ዋስትና የምዕራባውያን ስንዴ እንደሆነ ሲያስቡ፣ ኢትዮጵያ ግን በጀመረችው የበጋ ስንዴና ሰፋፊ የእህልና የአትክልት እርሻዎቿ ከራሷ አልፋ ለሌሎች ለመትረፍ ጫፍ ላይ ትገኛለች።
በአንድ ወቅት የአፍሪካ የቆሻሻ መጣያ ለመባል የደረሰችው አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን መልክ ልትይዝ ዳር ዳር እያለች ነው፡፡ ያጋጠሙን ፈተናዎች ብዙ ውድ ዋጋዎች አስከፍለውናል፡፡ እነርሱን ባሰብናቸው ቁጥር ያመናል፡፡
ካጣነው በላይ ግን ያገኘነው ይበልጣል፡፡ መከራው አልገታንም፤ ፈተናው አላሸነፈንም፡፡ ለዚህም ለፈጣሪ ብዙ ምስጋና እናቀርባለን።
ዶ/ር ዐብይ አህመድ

Leave a Reply