ሊካሄድ ለታሰበው…

ሊካሄድ ለታሰበው…

  • Post comments:0 Comments
ሊካሄድ ለታሰበው ሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ያሉ ባህላዊ የዕርቅና የሰላም ግንባታ እሴቶች ተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ።ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገር ወዳድነት ስሜት የሚችለውን ሁሉ አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርበታል።
 
ሀገራዊ ምክክሩ ጠንካራና ዘላቂ ብሄራዊ መግባባት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ አይቀርም። በመመካከርና በመነጋገር ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የቆዩ የቁርሾና ቂሞች በልማትና ዕድገት ላይ እያሳደሩ ያሉ ማነቆዎች በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት ያስችለናል።
 
ለዚህም ሀገራዊ ምክክሩ የታለመለት ግብ እንዲመታ በየማህበረሰቡ ዘንድ የሚገኙ ባህላዊ የዕርቅና ሰላም ግንባታ እሴቶች ተሞክሮ መውሰድና መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ጥርጥር የለውም።
 
ሀገሪቱ ላሉባት ችግሮች በዘላቂነት እልባት መስጠት የሚችል እንዲሆን የሁሉም ዜጎች ሀሳብና ተሳትፎ መረጋገጥ የሚገባው ሲሆን ለሂደቱ ደግሞ የሁሉም ባለድርሻ አካላትና ዜጎች አስተዋፅኦ አስፈላጊ ነው።
 
በተለይም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች የተጣለባቸውን አደራ በብቃት መወጣት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ለተሳትፎ ዝግጁ መሆንና ከውይይቱ የተሻለ ነገን ማየት እንደሚቻል አምኖ መግባት ለሂደቱ ስኬታማነቱ ይበጃል።
 
#prosperity

Leave a Reply