ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት…

ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት…

  • Post comments:0 Comments
ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት እርስ በእርስ በመከባበር፣ በመቻልና በመቻቻል፣ የእርስ በእርስ ትብብርን እና ድርድርን ዋጋ በሚያረጋግጥ የዜጎች መስተጋብር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት መሰረቱ መከባበር፣ መደማመጥ እና መቻቻል ነው።
አሁንም የውስጠ ፖለቲካችንን ተገዳዳሪ አቅም ከመከባበራችን እና ከመደማመጣችን አቅጣጫ መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ በብልፅግና እሳቤዎች ህዝባችንን ስንመራ በእርግጥም ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነትን ያስቀደመ አመራር ነው እያረጋገጥን ያለነው? ብለን ውስጠ ፖለቲካችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡
የግል ተጠቃሚነትና ስልጣንን ሽፋን ያደረገ ስርቆትና የተደራጀ ዘረፋ ባልተቀረፈበት የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ምን አይነት ወንድማማችነት ነው የሚረጋገጠው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ለራስ ጥቅም ሲባል የሚሰዋ የብልፅግና እሴት መኖር የለበትም፡፡
ወንድማማችነት እንኳንስ በህብረ-ብሄራዊ ደረጃ ይቅርና በቤተሰብና በስጋ ዝምድና ደረጃም ብርቱ ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ እርስ በእርስ መተዛዘንና መተሳሰብ፣ ለህዝባዊ እና አገራዊ ተልዕኮ ራስን የበለጠ ዝግጁ ማድረግ ለህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት መሰረት ነው፡፡

Leave a Reply