You are currently viewing በአንድ ወቅት…

በአንድ ወቅት…

  • Post comments:0 Comments

በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ጽንፈኝነትና አክራሪነት የሰው ልጆች በሰላምና በነጻነት ኑሯቸውን መምራት እንዳይችሉ፤በሕዝቦች ዘንድ እንዲሁም መከባበርና መቻቻል እንዳይኖር መሰናክል የሚሆን አስተሳሰብ እና ተግባር ነው” ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሊካሄድ ለታሰበው ሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ያሉ ባህላዊ የዕርቅና የሰላም ግንባታ እሴቶች ተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ። ነገን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገር ወዳድነት ስሜት የሚችለውን ሁሉ አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርበታል።

ሀገራዊ ምክክሩ ጠንካራና ዘላቂ ብሄራዊ መግባባት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ አይቀርም። በመመካከርና በመነጋገር ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የቆዩ የቁርሾና ቂሞች በልማትና ዕድገት ላይ እያሳደሩ ያሉ ማነቆዎች በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት ያስችለናል።

ምላሽ ይስጡ