የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው – ዶ/ር ቢቀላ ሁሪሳ

የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው – ዶ/ር ቢቀላ ሁሪሳ

  • Post comments:0 Comments

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የውጭ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ እያካሄደ ባለው የግምገማ፣የዕቅድ ትውውቅና ስልጠና መድረክ አንዱ አካል የሆነው የጉብኝት ፕሮግራም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በጉብኝት ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ቢቀላ ሁሬሳ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በዘጠና ቀን ዕቅድ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ኃላፊው በመልዕክታቸው ህዝቡ ለፓርቲው ካነሳቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች መካከል የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፣የዜጎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን የከተማ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ማሳካት መቻሉ ለሌሎች ክልሎች ተሞክሮ ነው ያሉ ሲሆን ይህ እንዲሳካ ለተጉ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በበኩላቸው ለዓመታት ሲጓተቱና የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ ጉዳዮችን ቅድሚያ በመስጠት እና በዘጠና ቀን ዕቅድ ውስጥ በማካተት ምላሽ ለመስጠት ተችሏል ያሉ ሲሆን በግንባታ ላይ ያሉ የመሰረተ ልማቶች አውታሮች እና የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ህዝቡን ለከፍተኛ ምሬት ሲዳርጉ መቆየቱን አውስተዋል፡፡

በጉብኝቱ በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚገነቡት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጨምሮ 300 ሜት ርዝመት ያለውና 45 ሜትር ስፋት ያለውን አዲሱን የዓባይ ድልድይ ፣ የናይል ማራቶን ዕቅድ እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሞላ መልካሙ፣የባህር ዳር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ የኔሰው መኮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply