ወጣቶች ለሃገር ግንባታ መነሻ የሚሆን ሃሳብ ማቅረብ እንጂ ለጥፋት ሃይሎች መጠቀሚያ መሳሪያ መሆን የለባቸውም፡-ዶ/ር ዓለሙ ስሜ

ወጣቶች ለሃገር ግንባታ መነሻ የሚሆን ሃሳብ ማቅረብ እንጂ ለጥፋት ሃይሎች መጠቀሚያ መሳሪያ መሆን የለባቸውም፡-ዶ/ር ዓለሙ ስሜ

  • Post comments:0 Comments

ወጣቶች ለሃገር ግንባታ መነሻ የሚሆን ሃሳብ ማቅረብ እንጂ ለጥፋት ሃይሎች መጠቀሚያ መሳሪያ መሆን የለባቸውም፡-ዶ/ር ዓለሙ ስሜ

ወጣቶች አገራችንን እያለማን አገር ለማፍረስ የሚሹ ሐይሎችን ደግሞ በጋራ በመመከት ለመጪው ትውልድ የበለጸገችና ሰላሟ የተረጋገጠች ሃገር ማስረከብ ይኖርብናል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በፓርቲው የሲቪክና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ተናገሩ፡፡

በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪነት በደብረ ብርሃን እየተካሄደ በሚገኘው አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት ኃላፊው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለሃገር ግንባታ እና ለቀጣይ ትውልድ መሰረት የሚሆን ስራ ነው ብለዋል፡፡

የገጠመንን ፈተና እያሸነፍን ብልጽግናችንን እንደምናረጋግጥ ጥርጥር የለውም ያሉት ዶ/ር ዓለሙ ሲሆን ሰላም አልሻም በማለት ገፍቶ የሚመጣ ሃይል ካለ በሚገባው ቋንቋ አስረድተን እንመልሰዋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ስራ ፕሬዝደንት ወጣት አስፋው ተክሌ በበኩሉ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ለነገዋ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጥል በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንሰጠዋለን ያሉ ሲሆን በአራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 6.3 ሚሊዬን ወጣቶችን በማስተባበር 2.2 ቢሊዬን ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየሰራች ባለችበት በዚህ ወቅት ጠላቶቿ አገርን ለማፍረስ ቢሰሩም በወጣቶች ጥረት ማንም ሐይል ከብልጽግና ጉዟችን ሊያስቆመን አይችልም ያለው ፕሬዝደንቱ በጠቅላይ ሚኒስትራችን የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬታማነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ ሚና አለውም ብለዋል፡፡

Leave a Reply