የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለት በደብረ ብርሀን ከተማ ይጀመራል

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለት በደብረ ብርሀን ከተማ ይጀመራል

  • Post comments:0 Comments

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለት በደብረ ብርሀን ከተማ ይጀመራል

ስብሰባው ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዋናነት በሊጉ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም ለቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል።

በተለይም ምግቤን ከጓሮዬ በተሰኘው የከተማ ግብርና እና በመሰል የወጣቶች ንቅናቄ የተሰሩ ስራዎችን መስክ ድረስ ወርዶ በመጎብኘት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚደረግ ከሊጉ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ከዚህም ጎን ለጎን ከ6 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የ2014 የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የሚካሄድ ይሆናል።

በተጨማሪም የወጣቶች ሊግ ጠቅላላ ሀገራዊ ጉባኤ የዝግጅት ስራዎችን የሚገመግም ሲሆን የሚካሄድበትን ጊዜ እና ቦታ በማዕከላዊ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎበት እንደሚወሰን የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፅ/ቤት ሀላፊ የሆነው ወጣት አክሊሉ ታደሰ ገልጿል።

Leave a Reply