ብልጽግና ፓርቲ ስብራቶችን…

ብልጽግና ፓርቲ ስብራቶችን…

  • Post comments:0 Comments

ብልጽግና ፓርቲ ስብራቶችን የሚጠግንና ሽንቁሮችን የሚደፍን ጠንካራ የፖሊሲ ሀሳቦችን ያቀረበ ፓርቲ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ከፓርቲው ጎን በመቆም የሰላም መሰረቶችን ለማጠንከር መስራት ይኖርብናል፡፡

መላው የአገራችን ህዝቦች የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን በብቃት በመመከት አገራችን የጀመረችውን የለውጥና የከፍታ ጉዞ በጽናት ለማስቀጠል በጋራ መታገል አለብን:: የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማረም፣ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባትና ብሄራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አራት አመታት በየደረጃው ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው::

ፓርቲያችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን፣ አብሮነትን፣ የአንዱ ስኬት የሌላው ስኬት፣ የአንዱ ህመም የሌላው ህመም እንደሆነና እድልና እጣፈንታችንም አንድ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ የፖሊሲ ሀሳቦችን ለኢትዮጵያዊያን ያቀረበ ፓርቲ ነው::

እንደ ሀገር ያደሩ ችግሮችን ለመፍታት ብልጽግና በቁርጠኝነት እየተሰራ ቢሆንም ችግሮቹ በአንድ ጀንበር የማይፈቱ ግን መጪው ግዜ ብሩህ ተስፋ የሚታይበት እንደሆነ ከወዲሁ መገንዘብ ያስችለናል::ብልጽግና ከእውነት ጋር መጋፈጥ መርሆው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን ችግርን በመሸሽ ሳይሆን ችግርን አውቆ በማከም ላይ ተመስርቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የብልጽግና እሳቤዎች ጥልቅ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩ፣ እውነትንና እውቀትን መሰረት ያደረጉ፣ የችግሩን መሰረት በጥልቀት የሚፈትሹና ለኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ ሁነኛ መፍትሄዎች በመሆናቸው ህዝቡ እነዚህን ሀቆች አውቆ ከብልጽግና ጎን መሰለፍ ይኖርበታል፡፡

ከብልጽግና ጋር መጓዝ አብሮነትን ማጠናከር፣ ወንድማማችነትን እውን ማድረግና አገርን ማከም ነው፤

Leave a Reply