ለትውልድ የሚተላለፍ አረንጓዴ ምንጣፍ  /በሚራክል እውነቱ/

ለትውልድ የሚተላለፍ አረንጓዴ ምንጣፍ /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ብላ የሰየመችውን ዓመታዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት ከአራት ዓመታት በፊት ማስጀመሯ ይታወሳል። በየዓመቱም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ስትተክል ቆይታለች።
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለመቋቋምና የአገራችንን ዕድገትና ብልፅግና በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል በችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች በመሳተፍ አገራችን እተገበረችው ያለውን አረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ለማስፋፋትና ለማሳደግ የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።
በመሆኑም ባለፈው የክረምት ወቅት 6 ቢሊዬን ችግኝ የተተከለ ሲሆን በዚህ አመት የክረምት ወራት በመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች 6 ቢሊዬን ችግኝ እንዲተከል የያዝነው ሀገራዊ ግብ እንዲሳካ በየደረጃው ያለው መዋቅራችን በበቂ ትኩረት ሊሳተፍ፣ሊመራና ሊያስተባብር ይገባል።
የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የተደራጀ እንቅስቃሴ ለማበረታታትና ለማነቃቃት እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ፣ የችግኝ ተከላ ቦታ በማዘጋጀት፣ ጉድጓድ በመቆፈር፣ ችግኝ በማዘጋጀትና የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ እንዲሳካ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ እነሆ ዛሬ ሊጀመር ሰዓቱ ደርሷል።
ዘንድሮ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሊተከል ከተዘጋጀው 6 ቢሊዬን ችግኝ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ተዘጋጅተዋል።ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአገር ውስጥ ባለፈ በጎረቤት አገራትም እንዲጀመር ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ለጎረቤት አገራት አበርክታለች።
ይህን ዓመታዊ አገር ዐቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለማከናወን ሰፊ ዝግጅት እያደረገች ስለመሆኑ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መግለጻቸው ይታወሳል።
በሦስት ዓመታት ውስጥ ከተተከሉት ችግኞችም በአማካኝ በአጠቃላይ 80 ነጥብ አምስት በመቶ የሚሆኑ ችግኞች መፅደቅ የቻሉ ሲሆን፣ ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ ተተክለው መፅደቅ ያልቻሉ እና በከብቶች ተነቅለው፣ ተረግጠው እና በሌሎች ምክንያቶችም መፅደቅ ያልቻሉ ናቸው።
በኢትዮጵያ የደን ልማት ለማጎልበት ያስችል ዘንድ «አረንጓዴ አሻራ» መርሃ ግብር ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግኞችን እንዲተክል «አሻራችንን በማኖር ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፍ እንዘርጋ» ሲሉ ጥሪ በማስተላለፍ አንድ ብሎ የጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘንድሮ “አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል አራተኛ ዙር ላይ ደርሰናል።

Leave a Reply